Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 25:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ዳዊትም ሰዎቹን፥ “በሉ ሁላችሁም ሰይፋችሁን ታጠቁ” አላቸው። ስለዚህ ሁሉም ሰይፋቸውን ታጠቁ፤ ዳዊትም የራሱን ታጠቀ። አራት መቶ ያህል ሰዎች ከዳዊት ጋር ሲወጡ መቶ ያህሉ ግን ጓዝ ለመጠበቅ ቀሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ዳዊትም ሰዎቹን፣ “በሉ ሁላችሁም ሰይፋችሁን ታጠቁ” አላቸው። ስለዚህ ሁሉም ሰይፋቸውን ታጠቁ፤ ዳዊትም የራሱን ታጠቀ። አራት መቶ ያህል ሰዎች ከዳዊት ጋራ ሲወጡ መቶ ያህሉ ግን ጓዝ ለመጠበቅ ቀሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ዳዊትም “በሉ ሰይፋችሁን ታጠቁ!” የሚል ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም እንደ ታዘዙት አደረጉ፤ ዳዊትም ራሱ ሰይፉን ታጠቀ፤ ጓዝ የሚጠብቁ ሁለት መቶ ሰዎች ወደ ኋላ ትቶ አራት መቶ ሰዎች በማስከተል ገሥግሦ ለመሄድ ተነሣ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዳዊ​ትም ሰዎ​ቹን፥ “ሁላ​ችሁ ሰይ​ፋ​ች​ሁን ታጠቁ” አላ​ቸው። ሁሉም ሰይ​ፋ​ቸ​ውን ታጠቁ፤ ዳዊ​ትም ሰይ​ፉን ታጠቀ፤ አራት መቶ ሰዎ​ችም ዳዊ​ትን ተከ​ት​ለው ወጡ፤ ሁለት መቶ​ውም በጓ​ዛ​ቸው ዘንድ ተቀ​መጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ዳዊትም ሰዎቹን፦ ሁላችሁ ሰይፋችሁን ታጠቁ አላቸው። ሁሉም ሰይፋቸውን ታጠቁ፥ ዳዊትም ሰይፉን ታጠቀ፥ አራት መቶ ሰዎችም ዳዊትን ተከትለው ወጡ፥ ሁለት መቶውም በዕቃው ዘንድ ተቀመጡ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 25:13
17 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ሰዎቹ ከቅዒላ ተነሥተው መሄድ ወደሚችሉበት ቦታ ሁሉ ሄዱ፤ ዳዊት ከቅዒላ መሸሹን በሰማ ጊዜ፥ ሳኦል ወደዚያ መሄዱን ተወ።


ባልንጀራህ ባሳፈረህ ጊዜ ኋላ እንዳትጸጸት ለሙግት ወደ ሽንጎ ፈጥነህ አትውጣ፥


ሰውን ጠቢብ አእምሮው ከቁጣ ያዘገየዋል፥ ለበደለኛውም ይቅር ይል ዘንድ ክብር ይሆንለታል።


ነፍስ እውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም፥ እግሩንም የሚያፈጥን ከመንገድ ይስታል።


ለትግሥተኛ ሰው ብዙ ማስተዋል አለው፥ ቁጡ ግን ስንፍናውን ከፍ ከፍ ያደርጋል።


የእስራኤልም አለቆች ከስንቃቸው ወሰዱ፥ የጌታንም ምሪት አልጠየቁም።


ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ ስሜቱን የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል።


የተጨነቁ፥ ዕዳ ያለባቸውና የተከፉ ወደ እርሱ ተሰባሰቡ፤ እርሱም መሪያቸውም ሆነ። እነርሱም አራት መቶ ያህል ሰዎች ነበሩ።


የዳዊት ሰዎችም ወደመጡበት ተመለሱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የተባሉትን ሁሉ ነገሩት።


ስለዚህ ዳዊትና አብረውት ያሉት ስድስት መቶ ሰዎች ተነሥተው የጋት ንጉሥ ወደ ሆነው ወደ ማዖክ ልጅ ወደ አኪሽ ሄዱ።


አገልጋዮቹ ሁሉ፥ ከሊታውያን፥ ፈሊታውያን እንዲሁም ከጌት አብረውት የመጡትን ስድስት መቶ ጌታውያን ሁሉን ጨምሮ ተሰልፈው በንጉሡ ፊት ዐለፉ።


ክፉ እመልሳለሁ አትበል፥ ጌታን ተማመን፥ እርሱም ያድንሃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios