Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 9:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ንጉሥ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱንና ሊሠራው የፈለገውን ሌላውንም ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና ቤተ መንግሥቱን ሠርቶ ከጨረሰና ለመሥራት የፈለገውንም ሁሉ ካከናወነ በኋላ፣

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ንጉሥ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱንና ሊሠራው የፈለገውን ሌላውንም ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከዚ​ህም በኋላ ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት፥ የን​ጉ​ሡን ቤትና ሰሎ​ሞን ያደ​ር​ገው ዘንድ የወ​ደ​ደ​ውን ሁሉ ሠርቶ በፈ​ጸመ ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት፥ የንጉሡን ቤትና ሰሎሞን የወደደውን የልቡን አሳብ ሁሉ ሠርቶ በፈጸመ ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 9:1
18 Referencias Cruzadas  

ሰሎሞን የግብጽን ንጉሥ ሴት ልጅ በማግባት ከንጉሡ ጋር ወዳጅነት መሠረተ፤ እርሷንም አምጥቶ ቤተ መንግሥቱን፥ የጌታን ቤትና የኢየሩሳሌምን ዙሪያ ቅጽር ሠርቶ እስኪጨርስ ድረስ በዳዊት ከተማ አኖራት።


የጌታ ቤት መሠረት የተጣለው በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ዚፍ ተብሎ በሚጠራው ወር ነበር።


ሰሎሞን ለራሱ የሚሆን ቤተ መንግሥት ሠራ፤ ቤተ መንግሥቱንም ለመሥራት ዐሥራ ሦስት ዓመት ፈጀበት።


የሊባኖስ ዱር የተባለ ቤተ መንግሥት ሠራ፤ ይህም ርዝመቱ መቶ ክንድ፥ ወርዱ አምሳ ክንድ፥ ቁመቱ ሠላሳ ክንድ ሲሆን፥ በአራት ረድፍ የቆሙ የዝግባ ምሰሶዎች ደግፈው የያዟቸው አግዳሚ የዝግባ ተሸካሚዎች ነበሩት።


ንጉሥ ሰሎሞን የጌታ ቤት ሁሉንም ሥራ ከፈጸመ በኋላ አባቱ ዳዊት ለጌታ ቤት አገልግሎት እንዲውል የለየውን ብሩን፥ ወርቁንና ሌላውንም ዕቃ በሙሉ በጌታ ቤት ግምጃ ቤት ውስጥ አኖረው።


በሚቀጥለውም ቀን ሰሎሞን ሕዝቡን ሁሉ አሰናበተ፤ ሁሉም ሰሎሞንን መረቁ፤ እግዚአብሔር ለአገልጋዩ ለዳዊትና ለሕዝቡ ለእስራኤል ስለ አደረገው በጎ ነገር ሁሉ ደስ ብሎአቸው ወደየቤታቸው ሄዱ።


ሰሎሞን ቤተ መቅደሱንና ቤተ መንግሥቱን ለመሥራት የፈጀበት ጊዜ ኻያ ዓመት ነበር።


የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዚህ ሁሉ ሥራ ለሰሎሞን የሚያስፈልገውን የሊባኖስ ዛፍና ዝግባ ከብዙ ወርቅ ጋር ሰጥቶት ነበር፤ ሥራውም ሁሉ ከተፈጸመ በኋላ ሰሎሞን በገሊላ ምድር የሚገኙትን ኻያ ታናናሽ ከተሞችን ለኪራም ሰጠው።


እነዚህም የስንቅ ማከማቻዎች፥ ፈረሶችና ሠረገሎች የሚጠበቁባቸው፥ ከተሞችን ከተመ፤ ሰሎሞንም በኢየሩሳሌም፥ በሊባኖስና በግዛቱ ሁሉ የሚፈልገውን ገነባ።


ሰሎሞንም ጸሎቱን በፈጸመ ጊዜ እሳት ከሰማይ ወርዶ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላውን መሥዋዕት በላ፤ የጌታም ክብር ቤቱን ሞላ።


ሰሎሞንም የጌታን ቤትና የንጉሡን ቤት ጨረሰ፤ በጌታ ቤትና በራሱ ቤት ለመሥራት በልቡ ያሰበውን ሁሉ አከናወነ።


እንዲህም ሆነ፤ ሰሎሞን የጌታን ቤትና የራሱን ቤት የሠራበት ሀያ ዓመት በተፈጸመ ጊዜ፥


ባዓላትንም፥ ለሰሎሞንም የነበሩትን ለግምጃ ቤት የሚያገለግሉ ከተሞች ሁሉ፥ የሠረገላውንም ከተሞች ሁሉ፥ የፈረሰኞችንም ከተሞች፥ በኢየሩሳሌምም በሊባኖስም በመንግሥቱም ምድር ሁሉ ሰሎሞን ለመሥራት የፈለገውን ሁሉ ሠራ።


ዐይኖቼ የፈለጉትን እንዳያዩ አልከለከልኋቸውም፥ ልቤም በድካሜ ሁሉ ደስ ይለው ነበርና ልቤን ከደስታ ሁሉ አላራቅሁትም፥ ከድካሜም ሁሉ ይህ እድል ፈንታዬ ሆነ።


ትልቅ ሥራን ሠራሁ፤ ለራሴ ቤቶችን ገነባሁ፥ ወይንንም ተከልሁ፥


በዐይን ማየት በምኞት ከመቅበዝበዝ ይሻላል፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos