Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 20:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ንጉሥ አክዓብም የሀገሪቱን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠርቶ “ይህ ሰው ምን ዓይነት ጠብ እንደሚፈልግ ተመልከቱ። ከዚህ በፊት ሚስቶቼንና ልጆቼን፥ ብሬንና ወርቄን እንዳስረክበው ጠይቆኝ ተስማምቼ ነበር” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የእስራኤልም ንጉሥ የአገሩን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠርቶ፣ “ይህ ሰው እንዴት ጠብ እንደሚፈልግ ታያላችሁ፤ ሚስቶቼንና ልጆቼን፣ ብሬንና ወርቄን እንዳስረክበው በጠየቀኝ ጊዜ አልከለከልሁትም” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ንጉሥ አክዓብም የሀገሪቱን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠርቶ “ይህ ሰው ምን ዐይነት ጠብ እንደሚፈልግ ተመልከቱ። ከዚህ በፊት ሚስቶቼንና ልጆቼን፥ ብሬንና ወርቄን እንዳስረክበው ጠይቆኝ ተስማምቼ ነበር” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ሚስቱ ኤል​ዛ​ቤ​ልም፥ “አሁ​ንም አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሆነህ እን​ደ​ዚህ ታደ​ር​ጋ​ለ​ህን? ተነሣ፤ እን​ጀ​ራ​ንም ብላ፤ ራስ​ህ​ንም አጽና፤ ልብ​ህም ደስ ይበ​ላት፤ የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ው​ንም የና​ቡ​ቴን የወ​ይን ቦታ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለ​ችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ሚስቱም ኤልዛቤል “አንተ አሁን የእስራኤልን መንግሥት ትገዛለህን? ተነሣ፤ እንጀራም ብላ፤ ልብህም ደስ ይበላት፤ የኢይዝራኤላዊውን የናቡቴን የወይን ቦታ እሰጥሃለሁ፤” አለችው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 20:7
18 Referencias Cruzadas  

አሁን ደግሞ ቤተ መንግሥትህንና የባለሥልጣኖችህን ቤት ሁሉ በርብረው ዋጋ ያለውን ንብረት ሁሉ ይዘው እንዲመጡ የጦር መኰንኖቼን እልካለሁ፤ እነርሱም ነገ ጧት በዚሁ ሰዓት እዚያ ይደርሳሉ።”


ሽማግሌዎቹና ሕዝቡም “እርሱ ለሚልህ ነገር ሁሉ ግምት አትስጠው፤ እሺም አትበለው” አሉት።


ሽማግሌዎችም ሁሉ ሕዝቡም ሁሉ፦ “አትስማው፥ እሺም አትበለው” አሉት።


ከዚህ በኋላ ሰሎሞን የዳዊት ከተማ ከሆነችው ከጽዮን የጌታን የቃል ኪዳን ታቦት ለማምጣት፥ ወደ ቤተ መቅደሱም ለማስገባት፥ የእስራኤል የነገድ መሪዎችና የጐሣ አለቆች ሁሉ እርሱ ወደሚገኝበት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ ጠራ።


የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ በቁጣ ልብሱን ቀደደ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ “የሶርያ ንጉሥ ይህን ሰው እንደምፈውስለት አድርጎ እንዴት ይገምታል? እኔ ሰውን ከቆዳ በሽታ እፈውስ ዘንድ የማዳንና የመግደል ሥልጣን ያለኝ እግዚአብሔር መሰልኩትን? በእርግጥ ይህ አባባል ከእኔ ጋር ጠብ መፈለጉን በግልጥ ያሳያል!” አለ።


ዳዊትም ከሻለቆችና ከመቶ አለቆች ከሹማምንቱም ሁሉ ጋር ተማከረ።


ዳዊትም የእስራኤልን አለቆች ሁሉ፥ የነገዶቹንም አለቆች፥ ንጉሡንም በክፍል የሚያገለግሉትን የሠራዊቱ አለቆች፥ ሻለቆቹንም፥ የመቶ አለቆቹንም፥ በንጉሥና በልጆቹ ሀብትና ግዛት ላይ የተሾሙትን፥ ጃንደረቦችንም፥ ጽኑዓን ኃያላኑንም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።


ጉዳትን ይፀንሳሉ፥ በደልንም ይወልዳሉ፥ ሆዳቸውም ተንኰልን ያዘጋጃል።”


አቤቱ፥ ከክፉ ሰው አድነኝ፥ ከዓመፀኞች ሰዎች ጠብቀኝ


የአፉ ቃል ግፍና ሽንገላ ነው፥ ማስተዋልን በጎ ማድረግንም ተወ።


እርሱ ብቻ ዓለቴና መድኃኒቴም ነው፥ እርሱ መጠጊያዬ ነው፥ በፍጹም አልታወክም።


የሞት መሣርያንም አሰናድቷል፥ ፍላጻዎቹንም የሚንበለበሉ አደረገ።


መልካም ምክር በሌለበት ሕዝብ ይወድቃል፥ በአማካሪዎች ብዛት ግን ዋስትና ይገኛል።


መልካምን ተግቶ የሚሻ ደስታን ይፈልጋል፥ ክፉን በሚፈልግ ግን ክፉ ይመጣበታል።


ልባቸው ግፍን ታስባለችና፥ ከንፈራቸውም ተንኮልን ትናገራለችና።


ጠማማነት በልቡ አለ፥ ሁልጊዜም ክፋትን ያቅዳል፥ ጠብንም ይዘራል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos