Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 20:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ቤንሀዳድም አክዓብን “አባቴ ከአባትህ የወሰዳቸውን ከተሞች እመልስልሃለሁ፤ አባቴ በሰማርያ እንዳደረገው ሁሉ አንተም በደማስቆ ለራስህ የንግድ ማእከል ልታቋቁም ትችላለህ” አለው። አክዓብም “እንግዲያውስ በዚህ ስምምነት መሠረት እኔም በነጻ እለቅሃለሁ” ሲል መለሰለት። አክዓብም በዚህ ዓይነት ከእርሱ ጋር የውል ስምምነት አድርጎ በነጻ እንዲሄድ ፈቀደለት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ቤን ሃዳድም፣ “አባቴ ከአባትህ የወሰዳቸውን ከተሞች እመልሳለሁ፤ አባቴ በሰማርያ እንዳደረገው ሁሉ፣ አንተም በደማስቆ የራስህን ገበያ ማቋቋም ትችላለህ” አለው። አክዓብም፣ “እንግዲያውስ ስምምነት አድርገን በነጻ እለቅቅሃለሁ” አለው፤ ስለዚህም ከርሱ ጋራ የውል ስምምነት አድርጎ ለቀቀው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ቤንሀዳድም አክዓብን “አባቴ ከአባትህ የወሰዳቸውን ከተሞች እመልስልሃለሁ፤ አባቴ በሰማርያ እንዳደረገው ሁሉ አንተም በደማስቆ ለራስህ የንግድ ማእከል ልታቋቊም ትችላለህ” አለው። አክዓብም “እንግዲያውስ በዚህ ስምምነት መሠረት እኔም በነጻ እለቅሃለሁ” ሲል መለሰለት። አክዓብም በዚህ ዐይነት ከእርሱ ጋር የውል ስምምነት አድርጎ በነጻ እንዲሄድ ፈቀደለት።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 20:34
12 Referencias Cruzadas  

ንጉሥ ቤንሀዳድም አሳ ባቀረበው ሐሳብ ተስማምቶ የጦር አዛዦቹንና ሠራዊቱን በመላክ በእስራኤል ከተሞች ላይ አደጋ እንዲጥሉ አደረገ፤ እነርሱም ዒዮን፥ ዳን፥ አቤልቤትማዕካና የገሊላ ባሕር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች በገሊላ ባሕር አጠገብ የሚገኘውን አገርና የንፍታሌምን ግዛት ሁሉ ያዙ።


የንጉሥ ቤንሀዳድ ባለሟሎች የምሕረት መልእክት ይጠባበቁ ስለ ነበር፥ አክዓብ “ወንድሜ” ሲል በሰሙ ጊዜ ወዲያውኑ ቀበል አድርገው “አንተ እንዳልከው ቤንሀዳድ በእርግጥ ወንድምህ ነው!” አሉት። አክዓብም “ወደ እኔ አምጡት!” አላቸው። ቤንሀዳድም በመጣ ጊዜ፥ አክዓብ ወደ ሠረገላው ገብቶ እንዲቀመጥ ቤንሀዳድን ጋበዘው።


ከዚህ በኋላ ያ ነቢይ ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “ጌታ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ ‘እኔ ይገደል’ ብዬ የፈረድኩበትን ሰው እንዲያመልጥ ስለ ፈቀድህ በእርሱ ፈንታ አንተ በሞት ትቀጣለህ፤ የዚያ ሰው ሠራዊት አምልጦ እንዲሄድ ስላደረገ ሠራዊትህም ይደመሰሳል።”


የሶርያ ንጉሥ “በንጉሡ ላይ እንጂ በሌላ በማንም ላይ አደጋ አትጣሉ” ሲል ለሠላሳ ሁለቱ የሠረገላ ጦር አዛዦች ትእዛዝ አስተላለፈ።


ወልደ አዴር ንጉሡን አሳን እሺ አለው፥ የሠራዊቱንም የጦር አዛዦች በእስራኤል ከተሞች ላይ ላከ፤ እነርሱም ዒዮንንና ዳንን፥ አቤልማይምንና ለንፍታሌም እንደ ግምጃ ቤት የሚያገለግሉትን ከተሞች ሁሉ ያዙ።


የሶርያም ንጉሥ የሰረገሎቹን አለቆች እንዲህ ብሎ አዝዞ ነበር፦ “ከእስራኤል ንጉሥ በቀር ትንሽ ቢሆን ወይም ትልቅ ከማናቸውም ጋር አትዋጉ።”


ክፉዎች እድል ቢሰጣቸው እንኳን ጽድቅን አይማሩም፤ በቅኖች ምድር ክፉን ነገር ያደርጋሉ፥ የጌታንም ግርማ አያዩም።


“እነዚህ ሰዎች፤ ‘አድማ’ ብለው የሚጠሩትን፤ ማንኛውንም ነገር፤ ‘አድማ’ አትበሉ፤ እነርሱ የሚፈሩትን አትፍሩ፤ አትሸበሩለትም።


ጌታ አምላክህም በእጅህ አሳልፎ በሰጣቸውና ድል በምትነሣበት ጊዜ፥ ፈጽመህ አጥፋቸው፥ ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ፥ አትማራቸውም፥


አሞናዊው ናዖስ ወጥቶ ያቢሽ ገለዓድን ከበባት፤ የያቢሽም ሰዎች ሁሉ ናዖስን፥ “ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፥ እኛም እንገዛልሃለን” አሉት።


የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን ከነሕይወቱ ማረከው፤ ሕዝቡን ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው።


ነገር ግን ሳኦልና ሠራዊቱ አጋግን፥ ምርጥ ምርጡን በግና የቀንድ ከብት፥ የሰባውን ጥጃና ጠቦት፥ መልካም የሆነውን ሁሉ ሳይገድሉ ተውት። እነዚህን ፈጽመው ለማጥፋት ፈቃደኞች አልነበሩም፤ ነገር ግን የተናቀውንና የማይጠቅመውን ሁሉ አጠፉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos