Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 18:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አክዓብ አብድዩን “ፈረሶችንና በቅሎዎችን ከሞት የምናድንበት በቂ ሣር እናገኝ እንደሆን በምድሪቱ ወደሚገኘው ምንጭና ወንዝ እስቲ ሂድና እይ፤ ምናልባት እንስሶቻችንን ከሞት ማዳን እንችል ይሆናል” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 አክዓብም አብድዩን፣ “ተነሣና በአገሪቱ ውስጥ ወዳሉት ምንጮችና ሸለቆዎች ሂድ፤ ፈረሶቻችንና በቅሎዎቻችን እንዳይሞቱ በሕይወት እንዲቈዩ ምናልባት ሣር እናገኝ ይሆናል።” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 አክዓብ አብድዩን “ፈረሶችንና በቅሎዎችን ከሞት የምናድንበት በቂ ሣር እናገኝ እንደሆን በምድሪቱ ወደሚገኘው ምንጭና ወንዝ እስቲ ሂድና እይ፤ ምናልባት እንስሶቻችንን ከሞት ማዳን እንችል ይሆናል” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 አክ​ዓ​ብም አብ​ድ​ዩን፥ “በሀ​ገሩ መካ​ከል ወደ ውኃ ምንጭ ሁሉና ወደ ፈፋ ሁሉ ና እን​ሂድ፤ እን​ስ​ሶ​ችም ሁሉ እን​ዳ​ይ​ጠፉ ፈረ​ሶ​ች​ንና በቅ​ሎ​ችን የም​ና​ድ​ን​በት ሣር ምና​ል​ባት እና​ገኝ እንደ ሆነ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አክዓብም አብድዩን “በአገሩ መካከል ወደ ውሃው ምንጭ ሁሉና ወደ ወንዝ ሁሉ ሂድ፤ እንስሶችም ሁሉ እንዳይጠፉ ፈረሶችንና በቅሎችን የምናድንበት ሣር ምናልባት እናገኛለን፤” አለው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 18:5
11 Referencias Cruzadas  

ኤልዛቤል የጌታን ነቢያት ታስገድል በነበረችበትም ጊዜ አብድዩ አንድ መቶ የሚሆኑትን የእግዚአብሔርን ነቢያት ከሁለት ከፍሎ ኀምሳ፥ ኀምሳውን በዋሻዎች ከሸሸጋቸው በኋላ እህልና ውሃ በማቅረብ ይመግባቸው ነበር።


እያንዳንዳቸው በአገሪቱ ወደየትኛው ክፍል ሄደው መፈለግ እንዳለባቸው ከተስማሙ በኋላ አክዓብና አብድዩ ለየብቻቸው በሁለት አቅጣጫ ተሰማሩ።


እንጀራን ከምድር ያወጣ ዘንድ ሣርን ለእንስሳ፥ ለምለሙንም ለሰው ልጆች ጥቅም ያበቅላል።


ታላላቆቻቸውም ብላቴኖቻቸውን ወደ ውኃ ላኩ፤ ወደ ጉድጓድ መጡ ውኃም አላገኙም፥ ዕቃቸውንም ባዶውን ይዘው ተመለሱ፤ አፈሩም ተዋረዱም ራሳቸውንም ተከናነቡ።


እንስሶች እጅግ ጮኹ፥ የላምም መንጎች ማሰማርያ የላቸውምና ተቅበዘበዙ፥ የበግም መንጎች እየተሰቃዩ ነው።


ፈሳሹ ውኃ ደርቆአልና፥ እሳቱም የምድረ በዳውን ማሰማርያ በልቶአልና የምድር አራዊት ወደ አንተ አለኸለኹ።


እናንተ የምድር እንስሶች ሆይ፥ የምድረ በዳው ማሰማርያ ለምልሞአልና፥ ዛፉም ፍሬውን አፍርቶአልና፥ በለሱና ወይኑም ኃይላቸውን ሰጥተዋልና አትፍሩ።


የሁለት ወይም የሦስት ከተሞች ሰዎች እየተንገዳገዱ ወደ አንዲት ከተማ ውኃ ለመጠጣት ሄዱ፥ ነገር ግን አልረኩም፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ።


የበለስ ዛፍ ባታብብም፥ በወይን ተክሎች ላይ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ምርት ቢቋረጥ፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ከብቶችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos