1 ነገሥት 18:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 እኩለ ቀን ሲሆን ኤልያስ “ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጸልዩ! እርሱ አምላክ አይደለም እንዴ እርሱ በሐሳብ ተውጦ ይሆናል! ወይም ራሱን ያዝናና ይሆናል! ወይም ወደ ሩቅ አገር ሄዶ ይሆናል! ወይም ተኝቶ ያንቀላፋ ይሆናልና እንዲነቃ ቀስቅሱት!” እያለ ያፌዝባቸው ጀመር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 እኩለ ቀንም ላይ ኤልያስ፣ “ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ እንጂ፤ አምላክ አይደለም እንዴ! ምናልባት በሐሳብ ተውጦ ወይም ሥራ በዝቶበት፣ አልያም በጕዞ ላይ ይሆናል፤ ተኝቶም ከሆነ ቀስቅሱት” እያለ ያፌዝባቸው ጀመር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 እኩለ ቀን ሲሆን ኤልያስ “ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጸልዩ! እርሱ አምላክ አይደለም እንዴ እርሱ በሐሳብ ተውጦ ይሆናል! ወይም ራሱን ያዝናና ይሆናል! ወይም ወደ ሩቅ አገር ሄዶ ይሆናል! ወይም ተኝቶ ያንቀላፋ ይሆናልና እንዲነቃ ቀስቅሱት!” እያለ ያፌዝባቸው ጀመር፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 በቀትርም ጊዜ ቴስብያዊው ኤልያስ፥ “አምላክ ነውና በታላቅ ቃል ጩኹ፤ ምናልባት ይጫወት ይሆናል፥ ወይም አሳብ ይዞት ይሆናል፥ ወይም ተኝቶ እንደ ሆነ መቀስቀስ ያስፈልገዋል” እያለ ይዘባበትባቸው ጀመር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 በቀትርም ጊዜ ኤልያስ “አምላክ ነውና በታላቅ ቃል ጩኹ፤ ምናልባት አሳብ ይዞታል፤ ወይም ፈቀቅ ብሎአል፤ ወይም ወደ መንገድ ሄዶአል፤ ወይም ተኝቶ እንደ ሆነ መቀስቀስ ያስፈልገዋል፤” እያለ አላገጠባቸው። Ver Capítulo |