1 ነገሥት 11:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ንጉሡም “ስለምን ትሄዳለህ? ወደ አገርህ ለመሄድ ያሰብከው ከቶ ምን ጎድሎብህ ነው?” አለው። ሀዳድም “ምንም የተጓደለብኝ ነገር የለም፤ ብቻ ወደ ትውልድ አገሬ እንድመለስ ፍቀድልኝ” ሲል ለንጉሡ መለሰ፤ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ፈርዖንም፣ “እዚህ ምን ጐደለብህና ነው ወደ አገርህ ለመግባት የፈለግኸው?” ሲል ጠየቀው። ሃዳድም፣ “ምንም የጐደለብኝ የለም፣ ብቻ እንድሄድ ፍቀድልኝ” አለ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ንጉሡም “ስለምን ትሄዳለህ? ወደ አገርህ ለመሄድ ያሰብከው ከቶ ምን ተጓድሎብህ ነው?” አለው። ሀዳድም “ምንም የተጓደለብኝ ነገር የለም፤ ብቻ ወደ ትውልድ አገሬ እንድመለስ ፍቀድልኝ” ሲል ለንጉሡ መለሰ፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ፈርዖንም፥ “እነሆ፥ ከእኔ ዘንድ ወደ ሀገርህ መሄድ የፈለግህ ምን አጥተህ ነው?” አለው። አዴርም፥ “አንዳች አላጣሁም፤ ነገር ግን ልሂድ” ብሎ መለሰ። አዴርም ወደ ሀገሩ ተመለሰ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ፈርዖንም “እነሆ፥ ከእኔ ዘንድ ወደ አገርህ መሄድ የፈለግህ ምን አጥተህ ነው?” አለው። እርሱም “አንዳች አላጣሁም፤ ነገር ግን ልሂድ፤” ብሎ መለሰ። ሃዳድም ወደ አገሩ ተመለሰ፤ ሃዳድም ያደረገው ክፉ ነገር ይህ ነው፤ እስራኤልን አስጨነቀ፤ በኤዶምያስም ላይ ነገሠ። Ver Capítulo |