1 ነገሥት 1:49 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)49 አዶንያስም የጠራቸው ሁሉ ፈሩ፥ ተነሥተውም እያንዳንዳቸው በየመንገዳቸው ሄዱ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም49 በዚህም አዶንያስና የጠራቸው እንግዶች በሙሉ ደንግጠው ተነሡ፤ በየአቅጣጫውም ተበታተኑ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም49 አዶንያስ የጠራቸው ተጋባዦች ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ እጅግ ፈሩ፤ ሁሉም ተነሡ፤ እያንዳንዱም በየፊናው ተበተነ፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)49 አዶንያስም የጠራቸው ሁሉ ፈሩ፤ ተነሥተውም እያንዳንዳቸው በየመንገዳቸው ሄዱ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)49 አዶንያስም የጠራቸው ሁሉ ፈሩ፤ ተነሥተውም እያንዳንዳቸው በየመንገዳቸው ሄዱ። Ver Capítulo |
መከራቸው ድንገት ይነሣልና፥ ከሁለቱ የሚመጣውን ጥፋት ማን ያውቃል? (የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው።) የነገሩትን የሚሰማ ልጅ ከጥፋት የራቀ ነው፥ የነገሩትን የሚቀበልን ሰው እግዚአብሔር ይቀበለዋል። ከንጉሥ አንደበት ምንምን ሐሰት ይነገራል አይባልም፥ ከአንደበቱም የሚወጣ ሐሰት የለም። የንጉሥ ቃል ሾተል ናት፥ ለጥፋት የተሰጠችውን ሰው ሰውነት ታጠፋዋለች እንጂ አንድ አካል ብቻ የምታጠፋ አይደለም። ሰይፈ መዓቱ ብትሳል ግን ከወገኑ ጋር ሰውን ታጠፋለች፥ ከአሞሮች ግልገል ወገን የማይበላ እስኪሆን ድረስ እንደ እሳት ነበልባል ታቃጥላለች።