Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 16:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እንደ እነርሱ ላሉትና ከእነርሱም ጋር በአገልግሎት ለሚደክሙ ሁሉ ታዘዙ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እንደ እነርሱ ላሉትና ከእነርሱም ጋራ በአገልግሎት ለሚደክሙ ሁሉ ታዘዙ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እንደእነዚህ ላሉት ሰዎችና ከእነርሱም ጋር በሥራ ለሚደክሙት ሁሉ እንድትታዘዙ አጥብቄ አሳስባችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እና​ን​ተም እንደ እነ​ዚህ ላሉ​ትና ከእኛ ጋር በሥራ ተባ​ብሮ ለሚ​ደ​ክም ሁሉ ትታ​ዘ​ዙ​ላ​ቸው ዘንድ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እንደ እነርሱ ላሉትና አብሮ ለሚሠራ ለሚደክምም ሁሉ እናንተም እንድትገዙ እለምናችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 16:16
20 Referencias Cruzadas  

መንፈስም በሠላሳው አለቃ በዓማሣይ ላይ ወረደ፥ እርሱም እንዲህ አለ፦ “ዳዊት ሆይ! እኛ የአንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ! እኛ ከአንተ ጋር ነን፤ አምላክህ ይረዳሃልና ሰላም ሰላም ለአንተ ይሁን፥ ለሚረዱህም ሰላም ይሁን።” ዳዊትም ተቀበላቸው፥ የጭፍራም አለቆች አደረጋቸው።


ከፀሐይ በታች በሚደክምበት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምንድነው?


በጌታ ሆነው ለሚደክሙ ለፕሮፊሞናና ለጢሮፊሞሳ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጌታ እጅግ ለደከመች ለተወደደች ለጠርሲዳ ሰላምታ አቅርቡልኝ።


በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚሠሩ ለፕሪስካና ለአኪላ ሰላምታ አቅርቡልኝ፤


ለእናንተ ብዙ ለደከመችው ለማሪያ ሰላምታ አቅርቡልኝ።


በክርስቶስ አብሮን ለሚሠራው ለኡርባኖንና ለምወደውም ለስታኺ ሰላምታ አቅርቡልኝ።


እግዚአብሔርም አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት የሚያደርጉትን፥ ቀጥሎም የመፈወስ ስጦታ ያላቸውን፥ ሰዎችን የመርዳት ስጦታ ያላቸውን፥ አስተዳዳሪዎችንና በተለያዩ ልሳኖች የሚናገሩትን ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ሰይሟል።


ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ ነንና፤ የእግዚአብሔር እርሻ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ።


እያንዳንዳችሁ በክርስቶስ ፍርሃት የተገዛችሁ ሁኑ።


አንተም ደግሞ በሥራዬ አብረህ የተጠመድህ እውነተኛ ሆይ! ከእኔ ጎን በመቆም ከቀለሜንጦስ ጋር አብረው በወንጌል ሥራ ተጋድለዋልና እነዚህን ሴቶችና የተቀሩትን በሕይወት መጽሐፍ የተጻፉትን ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩትን እንድትረዱአቸው እለምንሃለሁ።


በእግዚአብሔር በአባታችን ፊት የእምነታችሁን ሥራ፥ የፍቅራችሁን ድካም፥ በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን የተስፋችሁንም መጽናት እናስታውሳለን።


ወንድሞች ሆይ! ድካማችንንና ጥረታችንን ታስታውሱታላችሁ፤ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እየሰበክን በአንዳችሁም ላይ እንኳ ሸክም ላለመሆን ስንል ሌሊትና ቀን እንሠራ ነበር።


ወንድሞች ሆይ! በእናንተ መካከል የሚደክሙትን በጌታም የሚገዙአችሁን የሚገሥጹአችሁንም እንድታውቁ፥


በመልካም የሚያስተዳድሩ፥ በተለይም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙ ሽማግሌዎች፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።


ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም። እነርሱ እንደሚጠየቁበት አድርገው ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ፤ ይህንንም በደስታ እንጂ በኀዘን እንዳያደርጉት፥ አለበለዚያ አይጠቅማችሁም።


ለመሪዎቻችሁ ሁሉ፥ ለቅዱሳንም ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከኢጣልያ ያሉትም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።


እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመፀኛ አይደለምና።


እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።


ስለዚህ የእውነት የሥራ ተባባሪዎች እንድንሆን እንደነዚህ ያሉትን ልንቀበል ይገባናል።


በትዕግስት መጽናትህንና ስለ ስሜ መከራ መቀበልህን አውቃለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos