1 ዜና መዋዕል 9:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 ዕቃውም በቍጥር፥ ይገባና ይወጣ ነበርና ከእነዚህ እያንዳንዱ በመገልገያው ዕቃ ላይ ሹሞች ነበሩ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም28 ከእነርሱም አንዳንዶቹ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በኀላፊነት ይጠብቁ ነበር፤ ዕቃዎቹም በሚገቡበትና በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ ይቈጥሩ ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 ሌሎቹ ሌዋውያን በአምልኮ ጊዜ መገልገያ ለሆኑ ንዋያተ ቅድሳት ኀላፊዎች ነበሩ፤ በአገልግሎት ላይ በሚውሉበት ጊዜ እየቈጠሩ አውጥተው፥ አገልግሎታቸው ሲያበቃም እየቈጠሩ መልሰው ያስቀምጡአቸው ነበር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 ዕቃውንም በቍጥር ያገቡና ያወጡ ነበርና ከእነዚህ አንዳንዶቹ በማገልገያው ዕቃ ላይ ሹሞች ነበሩ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 ዕቃውም በቍር ይገባና ይወጣ ነበርና ከእነዚህ አንዳንዱ በማገልገያው ዕቃ ላይ ሹሞች ነበሩ። Ver Capítulo |