Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 6:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 በቀኙም የቆመ ወንድሙ አሳፍ ነበረ፤ አሳፍም የበራክያ ልጅ፥ የሳምዓ ልጅ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 እንዲሁም የሔማን ወንድም አሳፍ በስተ ቀኙ ሆኖ ያገለግል ነበር፤ አሳፍ የበራክያ ልጅ፣ የሳምዓ ልጅ፣

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 በቀኙ በኩል የቆመው የሁለተኛው የመዘምራን ቡድን መሪ አሳፍ ነበር፤ የእርሱም የቤተሰብ የትውልድ ሐረግ ከዚህ በታች በተመለከተው አኳኋን እስከ ሌዊ ይደርሳል፦ አሳፍ፥ በራክያ፥ ሺምዓ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 በቀ​ኙም የሚ​ቆ​መው ወን​ድሙ አሳፍ ነበረ፤ አሳ​ፍም የበ​ራ​ክያ ልጅ፥ የሳ​ምዓ ልጅ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 በቀኙም የቆመ ወንድሙ አሳፍ ነበረ፤ አሳፍም የበራክያ ልጅ፥ የሳምዓ ልጅ፥

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 6:39
33 Referencias Cruzadas  

መዘምራኑ፥ የአሳፍ ልጆች፥ አንድ መቶ አርባ ስምንት።


መዘምራኑ፦ የአሳፍ ልጆች፥ አንድ መቶ ሀያ ስምንት።


የአሳፍ የምስጋና መዝሙር።


ለመዘምራን አለቃ፥ በዋሽንት፥ የአሳፍ መዝሙር።


የአሳፍ መዝሙር። አቤቱ፥ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ፥ ቅዱሱን መቅደስህንም አረከሱ፥ ኢየሩሳሌምንም አፈራረሱአት።


ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ኤዶታም፥ የአሳፍ መዝሙር።


ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። የአሳፍ የምስጋና መዝሙር።


የአሳፍ መዝሙር። እግዚአብሔር ለእስራኤል እንዴት ቸር ነው፥ ልባቸው ንጹሕ ለሆነ።


አስቀድሞም በዳዊትና በአሳፍ ዘመን እግዚአብሔርን በዜማ ለማመስገንና ለማክበር የመዘምራን አለቆች ነበሩ።


ምስጋናውን በጸሎት ለመጀመር መሪ የነበረው የአሳፍ ልጅ፥ የዛብዲ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ማታንያ፤ ከወንድሞቹ ሁለተኛ የነበረው ባቅቡቅያ፤ የይዱቱን ልጅ፥ የጋላል ልጅ፥ የሻሙዓ ልጅ ዓብዳ።


ከኤሊጸፋንም ልጆች ሺምሪና ይዒኤል፥ ከአሳፍም ልጆች ዘካርያስና መታንያ፥


መዘምራንም የነበሩት ሌዋውያን ሁሉ፥ አሳፍና ኤማን ኤዶታምም ልጆቻቸውም ወንድሞቻቸውም፥ ጥሩ በፍታ ለብሰው ጽናጽልና በገና መሰንቆም ይዘው በመሠዊያው አጠገብ በምሥራቅ በኩል ቆመው ነበር፤ ከእነርሱም ጋር መቶ ሀያ መለከት የሚነፉ ካህናት ነበሩ፤


የአሳፍ መዝሙር። እግዚአብሔር በመለኮታዊ ጉባኤ ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።


ለመዘምራን አለቃ፥ በመለከቶች፥ ስለ አሦራውያን፥ የአሳፍ የምስክር መዝሙር።


የአሳፍ ትምህርት። ሕዝቤ ሆይ፥ ሕጌን አድምጡ፥ ጆሮአችሁንም ወደ አፌ ቃል አዘንብሉ።


ለመዘምራን አለቃ፥ በበገናዎች፥ ስለ አሦራውያን፥ የአሳፍ የምስጋና መዝሙር።


የአሳፍ ትምህርት። አቤቱ፥ ስለምን ለሁልጊዜ ጣልኸኝ? በማሰማርያህ በጎች ላይስ ቁጣህ ስለምን ጨሰ?


የአሳፍ መዝሙር። የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ፥ ከፀሓይም መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ምድርን ጠራት።


መለከት የያዙ ጥቂት የካህናቱ ልጆች፥ የአሳፍ ልጅ፥ የዛኩር ልጅ፥ የሚካያ ልጅ፥ የማታንያ ልጅ፥ የሸማዕያ ልጅ፥ የዮናታን ልጅ ዘካርያስ፥


በእግዚአብሔር ቤት ሥራ ላይ ከነበሩ መዘምራን ከአሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ፥ የማታንያ ልጅ፥ የሓሻብያ ልጅ፥ የባኒ ልጅ ዑዚ በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ነበረ።


ግንበኞቹም የጌታን መቅደስ መሠረቱ፤ ካህናቱ ሙሉ ልብስ ለብሰው፥ መለከት ይዘው፥ የአሳፍ ልጆች ሌዋውያን ጸናጽል ይዘው በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት መመሪያ መሠረት ጌታን እንዲያመሰግኑ መረጧቸው።


የአሳፍም ልጆች መዘምራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሣፍም እንደ ኤማንም የንጉሡም ባለ ራእይ እንደነበረው እንደ ኤዶታም ትእዛዝ በየስፍራቸው ነበሩ፤ የደጁም ጠባቂዎች በሮቹን ሁሉ ይጠብቁ ነበር፤ ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ያዘጋጁላቸው ነበርና ከአገልግሎታቸው እንዲርቁ አያስፈልጋቸውም ነበር።


ንጉሡም ሕዝቅያስና ሹማምንቱ ሌዋውያንን በዳዊትና በባለ ራእዩ በአሳፍ ቃል ጌታን እንዲያመሰግኑ አዘዙ። በደስታም እያመሰገኑ፥ አጐነበሱም ሰገዱም።


የጌታም መንፈስ ከአሳፍ ወገን በነበረው በሌዋዊው በማታንያ ልጅ በይዒኤል ልጅ በበናያስ ልጅ በዘካርያስ ልጅ በየሕዝኤል ላይ በጉባኤው መካከል መጣ፤


የደጁም ጠባቂዎች ምድባቸው እንደዚህ ነበር፤ ከቆሬያውያን ከአሳፍ ልጆች የቆሬ ልጅ ሜሱላም።


ከአሳፍ ልጆች፤ ዘኩር፥ ዮሴፍ፥ ነታንያ፥ አሸርኤላ ነበሩ፤ እነዚህ የአሳፍ ልጆች በንጉሡ ትእዛዝ ትንቢት ከተናገረው ከአሳፍ ትእዛዝ በታች ነበሩ።


በዚያም ቀን ዳዊት በአሳፍና በወንድሞቹ አንደበት ጌታን እንዲያመሰግኑ አስቀድሞ ትእዛዝን ሰጠ።


የይስዓር ልጅ፥ የቀዓት ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥ የእስራኤል ልጅ ነበር።


የሚካኤል ልጅ፥ የበዓሤያ ልጅ፥ የመልክያ ልጅ፥


ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎች ለማገልገል ለዩ፤ በአገልግሎታቸውም ሥራ ይሠሩ የነበሩት ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።


ለቀዓትም ወገኖች ዕጣ ወጣ፤ ሌዋውያንም ለነበሩ ለካህኑ ለአሮን ልጆች ከይሁዳ ነገድ፥ ከስምዖንም ነገድ፥ ከብንያምም ነገድ ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ወሰዱ።


ከይሁዳም ልጆች ነገድ ከስምዖንም ልጆች ነገድ በስማቸው የተጠሩትን እነዚህን ከተሞች ሰጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios