Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 6:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ጌታም ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን በናቡከደነፆር እጅ ባስማረከ ጊዜ ኢዮሴዴቅ ተማርኮ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እግዚአብሔር የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በናቡከደነፆር እጅ ተማርከው እንዲወሰዱ ባደረገ ጊዜ ኢዮሴዴቅም ዐብሮ ተማርኮ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እግዚአብሔር የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በናቡከደነፆር ተማርከው በስደት እንዲኖሩ ባደረገ ጊዜ ኢዮጼዴቅም ከእነርሱ ጋር ተማርኮ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ኢዮ​ሴ​ዴ​ቅም፥ ይሁ​ዳና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ በተ​ማ​ረኩ ጊዜ ተማ​ርኮ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እግዚአብሔርም ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን በናቡከደነፆር እጅ ባስማረከ ጊዜ ኢዮሴዴቅ ተማርኮ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 6:15
17 Referencias Cruzadas  

ለይሁዳ ገዢ ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤል፥ ለታላቁ ካህን ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለኢያሱ፥ ለቀሩትም ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦


በንጉሡ በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የጌታ ቃል በነቢዩ በሐጌ እጅ ወደ ይሁዳ ገዢ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤልና ወደ ታላቁ ካህን ወደ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲል መጣ፦


የሠራዊቱ አዛዥ ናቡዛርዳን ሊቀ ካህናቱን ሤራያን በማዕረግ የእርሱ ምክትል የሆነውን ካህኑን ሶፎንያስና ሦስቱን የቤተ መቅደስ ዘበኞች እስረኛ አድርጎ ወሰዳቸው፤


ጌታም የይሁዳን ገዢ የሰላትያልን ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስ፥ የታላቁን ካህን የኢዮሴዴቅን ልጅ የኢያሱን መንፈስና የቀሩትንም ሕዝብ ሁሉ መንፈስ አስነሣ፤ መጥተውም የአምላካቸውን የሠራዊትን ጌታ ቤት ሠሩ።


ንጉሡም በዚያ እነርሱን አስደብድቦ በማሠቃየት በሞት ቀጣቸው። በዚህም ዓይነት የይሁዳ ሕዝብ ከአገራቸው ተማርከው ተወሰዱ።


አሕዛብ እንዲታዘዙ ክርስቶስ በቃልና በሥራ፥ በእኔ አድርጎ ከሠራው በቀር ምንም ልናገር አልደፍርም፤


በደረሱም ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ ለአሕዛብም የሃይማኖትን ደጅ እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ።


የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና ታላቁ ካህን የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፥ የቀሩትም ሕዝብ ሁሉ የአምላካቸውን የጌታን ድምፅ የነቢዩንም የሐጌን ቃል ሰሙ፥ አምላካቸው ጌታ ልኮታልና፤ ሕዝቡም በጌታ ፊት ፈሩ።


ናቡከደነፆር ማርኮ ያፈለሰው የሕዝብ ቍጥር ብዛት ይህ ነው፤ በሰባተኛው ዓመት ሦስት ሺህ ሀያ ሦስት አይሁድ፤


የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን በከተማይቱ የቀሩትን ሕዝብ፥ ወደ እርሱም ኮብልለው የነበሩትን ሰዎች፥ የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማርኮ አፈለሳቸው።


በዚያን ጊዜ የሸአልቲኤል ልጅ ዘሩባቤል የዮፃዳቅም ልጅ ኢያሱ ተነሥተው በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመሩ፤ የሚያግዙአቸው የእግዚአብሔር ነቢያት ከእነርሱ ጋር ነበሩ።


ይሁን እንጂ እነርሱ ለዘለዓለም ፈጽሞ እንዲደመሰሱ ደግሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ አልነበረም፤ ስለዚህም በዳግማዊ ኢዮርብዓም አማካይነት አዳናቸው።


እርሱም፦ “ጌታ ሆይ፥ ሌላ ሰው ላክ” አለ።


ዓዛርያስም ሠራያን ወለደ፤ ሠራያም ኢዮሴዴቅን ወለደ፤


የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ነበሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios