Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 26:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እንደ ወንድሞቻቸው ሆነው በጌታ ቤት እንዲያገለግሉ በየአለቆቻቸው የደጁ ጠባቂዎች ሰሞነኞች እነዚህ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የቤተ መቅደሱም ጠባቂዎች በአለቆቻቸው ሥር ተመድበው ልክ እንደ ቤተ ዘመዶቻቸው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ ለማከናወን ምድብ ተራ ነበራቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎች በየቤተሰቡ በቡድን ተከፍለው ነበር፤ እነርሱም ልክ እንደ ሌሎቹ ሌዋውያን በቤተ መቅደሱ ውስጥ አገልግሎት ነበራቸው፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እንደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሆነው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ የበ​ረ​ኞች አለ​ቆች በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው የሚ​ጠ​ብቁ እነ​ዚህ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እንደ ወንድሞቻቸው ሆነው በእግዚአብሔር ቤት ያገልግሉ ዘንድ የበረኞች የአለቆች ሰሞነኞች እነዚህ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 26:12
7 Referencias Cruzadas  

ከዚያም በኋላ ከሶርያውያን ሰፈር በመነሣት ወደ ሰማርያ ተመልሰው ሄዱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የከተማይቱን ቅጽር በር ዘበኞች ጠርተው “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ያየነው ሰው ወይም የሰማነው ድምፅ እንኳ የለም፤ ፈረሶችና አህዮች እንደ ታሰሩ ናቸው፤ ድንኳኖቹም ሶርያውያን ትተዋቸው ስለ ሄዱ ባዶአቸውን ናቸው” ሲሉ ነገሩአቸው።


ታናሹ እንደ ታላቁ፥ አስተማሪው እንደ ተማሪው፥ ሁሉም በተመሳሳይ መልኩ፥ ለሰሞናቸው ዕጣ ተጣጣሉ።


ሁለተኛውም ኬልቅያስ፥ ሦስተኛው ጥበልያ፥ አራተኛው ዘካርያስ ነበሩ፤ የሖሳ ልጆችና ወንድሞች ሁሉ ዐሥራ ሦስት ነበሩ።


በበሩም ሁሉ ለማገልገል በየአባቶቻቸው ቤቶች ታናሹና ታላቁ በተመሳሳይ መልኩ ይዕጣ ተጣጣሉ።


እነርሱና ልጆቻቸውም በጌታ ቤት በድንኳኑ ደጆች ላይ ዘበኞች ነበሩ።


የሌዋዊውም የይምና ልጅ የምሥራቁ ደጅ ጠባቂ ቆሬ የጌታን መባና የተቀደሱትን ነገሮች እንዲያከፋፍል ሕዝቡ ለጌታ በፈቃድ ባቀረቡት መባ ላይ ተሾመ።


የአሳፍም ልጆች መዘምራን እንደ ዳዊት፥ እንደ አሣፍም እንደ ኤማንም የንጉሡም ባለ ራእይ እንደነበረው እንደ ኤዶታም ትእዛዝ በየስፍራቸው ነበሩ፤ የደጁም ጠባቂዎች በሮቹን ሁሉ ይጠብቁ ነበር፤ ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ያዘጋጁላቸው ነበርና ከአገልግሎታቸው እንዲርቁ አያስፈልጋቸውም ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos