Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 2:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የይሁዳ ልጆች፤ ዔር፥ አውናን፥ ሴሎም ናቸው፤ እነዚህ ሦስቱ ከከነዓናዊቱ ሴዋ የተወለዱለት ልጆች ናቸው። የይሁዳም የበኩር ልጅ ዔር በጌታ ፊት ክፉ ነበረ፤ እርሱም ገደለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የይሁዳ ወንዶች ልጆች፤ ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፤ እነዚህን ሦስቱን ከከነዓናዊት ሚስቱ ከሴዋ ወለደ። የበኵር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ሆነ፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ይሁዳ ከከነዓናዊት ሚስቱ ከባትሹዓ ዔር፥ ኦናንና ሼላ ተብለው የሚጠሩ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ የበኲር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ስለ ነበር እግዚአብሔር በሞት ስለ ቀሠፈው፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የይ​ሁዳ ልጆች፤ ዔር፥ አው​ናን፥ ሴሎም፤ እነ​ዚህ ሦስቱ ከከ​ነ​ዓ​ና​ዊቱ ሴት ከሴዋ ልጅ ተወ​ለ​ዱ​ለት። የይ​ሁ​ዳም የበ​ኵር ልጅ ዔር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ ገደ​ለ​ውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የይሁዳ ልጆች፤ ዔር፥ አውናን፥ ሴሎም፤ እነዚህ ሦስቱ ከከነዓናዊቱ ከሴዋ ልጅ ተወለዱለት። የይሁዳም የበኵር ልጅ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ ገደለውም።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 2:3
8 Referencias Cruzadas  

የይሁዳም ልጆች፥ ዔር፥ ኦውናን፥ ሴላ፥ ፋሬስ፥ ዛራሕ፥ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ፥ የፋሬስም ልጆች ኤስሮም፥ ሐሙል።


ዳን፥ ዮሴፍ፥ ብንያም፥ ንፍታሌም፥ ጋድ፥ አሴር ናቸው።


የይሁዳ ልጆች ፋሬስ፥ ኤስሮም፥ ከርሚሆር፥ ሦባል ናቸው።


የይሁዳም ልጅ የሴሎም ልጆች የሌካ አባት ዔር፥ የመሪሳ አባት ለዓዳ፥ ከአሽቤዓ-ቤት የሚሆኑ ጥሩ በፍታ የሚሠሩ ወገኖች፥


ከሴሎናውያንም በኩሩ ዓሣያና ልጆቹ በዚያ ተቀመጡ።


የይሁዳ ልጆች ዔርና አውናን ናቸው፤ ዔርና አውናንም በከነዓን ምድር ሞቱ።


በየወገናቸው የይሁዳም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ከሴሎም የሴሎማውያን ወገን፥ ከፋሬስ የፋሬሳውያን ወገን፥ ከዛራ የዛራውያን ወገን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos