Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 17:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ከእስራኤል ሁሉ ጋር ባለፍሁበት ስፍራ ሁሉ፦ “ቤትን ከዝግባ እንጨት ለምን አልሠራችሁልኝም?” ብዬ ሕዝቤን እንዲጠብቁ ላዘዝኳቸው ለማናቸውም ለእስራኤል ፈራጆች በውኑ ተናግሬአለሁን?’

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በእስራኤላውያን ሁሉ መካከል ባለፍሁባቸው ቦታዎች ሁሉ፣ ሕዝቤን እንዲጠብቁ ካዘዝኋቸው መሪዎቻቸው “ለምን ከዝግባ ዕንጨት ቤት አልሠራችሁልኝም” ያልሁት አለን?’

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በተጓዝኩበት ዘመን ሁሉ እኔ ከሾምኳቸው መሪዎች መካከል አንዱን እንኳ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ቤተ መቅደስ እንዲሠራልኝ የጠየቅሁት አለን?’

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ጋር ባለ​ፍ​ሁ​በት ስፍራ ሁሉ፥ ስለ ምን ቤትን ከዝ​ግባ እን​ጨት አል​ሠ​ራ​ች​ሁ​ል​ኝም? ብዬ ሕዝ​ቤን ይጠ​ብቅ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ፈራ​ጆች ላዘ​ዝ​ሁት ለአ​ንዱ በውኑ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ከእስራኤል ሁሉ ጋር ባለፍሁበት ስፍራ ሁሉ “ስለ ምን ቤትን ከዝግባ አንጨት አልሠራችሁልኝም?” ብዬ ሕዝቤን ይጠብቅ ዘንድ ከእስራኤል ፈራጆች ላዘዝሁት ለአንዱ በውኑ ተናግሬአለሁን?’

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 17:6
19 Referencias Cruzadas  

ከእስራኤላውያን ሕዝብ ጋር በተጓዝሁበት ስፍራ ሁሉ ሕዝቤን እስራኤልን እንዲጠብቁ ካዘዝኋቸው መሪዎቻቸው አንዱን፥ ‘ከዝግባ ዕንጨት ለምን ቤት አልሠራህልኝም?’ ያልሁት አለን?


‘ሕዝቤን እስራኤልን ከግብጽ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ፥ ስሜ የሚጠራበት ቤተ መቅደስ የሚሠራበት በመላው እስራኤል ምንም ዓይነት ከተማ አልመረጥኩም፤ አሁን ግን በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ዳዊትን መርጫለሁ።’


አስቀድሞ ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን የምታወጣና የምታገባ አንተ ነበርህ፤ ጌታ አምላክህም፦ ‘ሕዝቤን እስራኤልን አንተ ትጠብቃለህ፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ አለቃ ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር።”


አሁንም ባርያዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ እንድትሆን አንተን ከማሰማርያው፥ ከበግ እረኝነት ወሰድሁህ።


የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሣላቸዋለሁ፥ ዳግመኛም አይፈሩምና አይደነግጡም፥ ከእነርሱም አንድም አይጐድልም፥ ይላል ጌታ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፥ እረኞቹንም እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ራሳቸውን ለመገቡ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞች በጎችን ማሰማራት አይገባቸውምን?


ይህም ሰላም ይሆናል፤ አሦር ወደ ምድራችን ከመጣ፥ ምሽጎቻችንንም ከረገጠ፥ ሰባት እረኞችና ስምንት አለቆች እናስነሣበታለን።


“በይሁዳ ምድር የምትገኚ አንቺ ቤተልሔም፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መሪ ከአንቺ ይወጣልና።”


ከዚህም በኋላ እስከ ነቢዩ እስከ ሳሙኤል ድረስ አራት መቶ አምሳ ዓመት ያህል መሳፍንትን ሰጣቸው።


የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖት ጋር ምን ስምምነት አለው? እኛ እኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሯል፥ በእነርሱ እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።


ጌታ እግዚአብሔር ሊያድንህ ጠላቶችህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥ በሰፈርህ መካከል ይሄዳልና ስለዚህ ነውረኛ ነገር እንዳያይብህ፥ ፊቱንም ከአንተ እንዳይመልስ ሰፈርህ የተቀደስ ይሁን።”


“በኤፌሶን ወዳለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፥ በቀኝ እጁ ሰባቱን ከዋክብት የያዘው በሰባቱም የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚመላለሰው እንዲህ ይላል፦


ከዚያም ጌታ ይሩበኣልን፥ ባርቅን፥ ዮፍታሔንና ሳሙኤልን ልኮ በሰላም ትኖሩ ዘንድ በዙሪያችሁ ካሉት ጠላቶቻችሁ እጅ ታደጋችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos