Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 17:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 አሁንም፥ አቤቱ፥ ስለ ባርያህና ስለ ቤቱ የተናገርኸው ቃል ለዘለዓለም የጸና ይሁን፤ እንደ ተናገርህም አድርግ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 “እግዚአብሔር ሆይ፤ አሁንም ለባሪያህና ለቤቱ የሰጠኸውን ተስፋ ለዘላለም የጸና ይሁን፤ እንደተናገርኸውም ፈጽም፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ስለ እኔና ስለ ዘሮቼ የተናገርከውን የተስፋ ቃል ሁሉ ፈጽም፤ አደርጋለሁ ያልከውንም ሁሉ አድርግ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 አሁ​ንም፥ አቤቱ፥ ስለ ባሪ​ያ​ህና ስለ ቤቱ የተ​ና​ገ​ር​ኸው ቃል ለዘ​ለ​ዓ​ለም የታ​መነ ይሁን፤ እንደ ተና​ገ​ር​ህም አድ​ርግ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 አሁንም፥ አቤቱ! ስለ ባሪያህና ስለ ቤቱ የተናገርኸው ለዘላለም የጸና ይሁን፤ እንደ ተናገርህም አድርግ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 17:23
10 Referencias Cruzadas  

ማርያምም፦ “እነሆኝ የጌታ አገልጋይ፤ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ፤” አለች። መልአኩም ከእርሷ ተለይቶ ሄደ።


ይህ ዛሬ እንደሆነ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለአባቶቻችሁ እንድሰጣቸው የማልሁትን መሐላ እንዳጸና ነው።” እኔም፦ “አቤቱ! አሜን” ብዬ መለስሁለት።


ለባርያህ የሰጠኸውን የተስፋ ቃልህን አስብ።


አንተም፦ ‘በእርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፥ ዘርህንም ከብዛቱ የተነሣ እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደርጋለሁ’ ብለህ ነበር።”


ሕዝብህንም እስራኤልን ለዘለዓለም ሕዝብህ አደረግኸው፤ አንተም፥ አቤቱ፥ አምላክ ሆነኸዋል።


ስምህ፦ ‘የሠራዊት ጌታ እርሱ የእስራኤል አምላክ ነው፥ በእውነት የእስራኤል አምላክ ነው’ በሚለው ውስጥ ለዘለዓለም ጽኑና ታላቅ ይሆናል፤ የባርያህም የዳዊት ቤት በፊትህ ጸንቶአል።


ነገር ግን የእስራኤል አምላክ ጌታ በእስራኤል ላይ የዘለዓለም ንጉሥ እንድሆን ከአባቴ ቤት ሁሉ መርጦኛል፤ ይሁዳንም አለቃ እንዲሆን መርጦታል፤ ከይሁዳም ቤት የአባቴን ቤት መርጦአል፤ ከአባቴም ልጆች መካከል በእስራኤል ሁሉ ላይ ሊያነግሠኝና ሊመርጠኝ ወደደ።


አሁንም የእስራኤል አምላክ ሆይ! አገልጋይህ ለነበረው ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ሁሉ እንዲፈጸም አድርግ።


አሁንም፥ አቤቱ አምላክ ሆይ! ቁጥሩ እንደ ምድር ትቢያ በሆነው በብዙ ሕዝብ ላይ አንግሠኸኛልና ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃልህ ይጽና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios