Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 17:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ይህም የሆነው በእስራኤል ላይ ፈራጆች ባሥነሣሁ ጊዜ ነበር፤ ጠላቶችህንም ሁሉ በሥርህ እንዲገዙ አደርለሁ። ጌታ ደግሞ ቤት እንደሚሠራልህ እነግርሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከዚህ ቀደም በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪዎች በሾምሁ ጊዜ ጨቋኞቹ ያደረጉትን ዛሬ አያደርጉትም፤ ጠላቶቻችሁን ሁሉ አዋርዳቸዋለሁ። “ ‘እግዚአብሔር ቤት እንደሚሠራልህ በግልጽ እነግርሃለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈራ​ጆ​ችን ካስ​ነ​ሣ​ሁ​በት ጊዜ ጀምሮ ጠላ​ቶ​ች​ህን ሁሉ አዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አን​ተ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደግሞ ቤትን ይሠ​ራ​ል​ሃል።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 17:10
16 Referencias Cruzadas  

ለሕዝቤ ለእስራኤል መሪዎች ከሾምሁለት ጊዜ አንሥቶ እንዳደረጉበት ከእንግዲህ አያደርጉበትም፤ ከጠላቶችህ ሁሉ አሳርፍሃለሁ። ከዚህም በላይ ጌታ ራሱ ቤት እንደሚሠራልህ ይነግርሃል፤


ወደ አባቶችህም ለመሄድ ዕድሜህ በተፈጸመ ጊዜ ከልጆችህ የሚሆነውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፤ መንግሥቱንም አጸናለሁ።


ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራን እሰጠዋለሁ፥ በዚያም እተክለዋለሁ፥ በስፍራውም ይቀመጣል፥ ከዚያም በኋላ አይናወጥም፤ ከእንግዲህም ወዲያ እንደ ቀድሞው ዘመን ዓመፀኞች አያስጨንቁትም፤


የዳዊት መዝሙር። ጌታ ጌታዬን፦ “ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው።”


የዕርገት መዝሙር። ጌታ ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፥ ጌታ ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።


ጠላት በእርሱ ላይ አይጠቀምም፥ የዓመፃ ልጅም መከራ አይጨምርበትም።


አዋላጆቹ እግዚአብሔርን ስለ ፈሩ ቤተሰብን ሰጣቸው።


ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ ሥር እስከሚያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና።


ጌታ በእስራኤላውያን ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ስለዚህ ለመስጴጦምያ ንጉሥ ለኩሽን-ሪሽዓታይም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እስራኤላውያንም ለኩሽን-ሪሽዓታይም ስምንት ዓመት በባርነት ተገዙለት።


እርሱም ዘጠኝ መቶ የብረት ሠረገሎች ስለ ነበሩት እስራኤላውያንን ሃያ ዓመት እጅግ አስጨነቃቸው፤ እነርሱም ይረዳቸው ዘንድ ወደ ጌታ ጮኹ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos