Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 12:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ዳዊትም ሊገናኛቸው ወጣ እነርሱንም እንዲህ አላቸው፦ “እኔን ለመርዳት በሰላም ወደ እኔ መጥታችሁ እንደሆነ ልቤ ከእንናተ ጋር አንድ ይሆናል፤ ለጠላቶቼ አሳልፋችሁ ልትሰጡኝ መጥታችሁ እንደሆነ ግን፥ በእጄ ዓመጽ የለብኝምና የአባቶቻችን አምላክ ይመልከት፤ ፍርድም ይስጥ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ዳዊትም እነዚህን ሰዎች ሊቀበል ወጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “የመጣችሁት ልትረዱኝና በሰላም ከሆነ፣ ከእኔ ጋራ እንድትሰለፉ ልቀበላችሁ ዝግጁ ነኝ፤ ነገር ግን እጄ ከበደል ንጹሕ ሆኖ ሳለ፣ ለጠላቶቼ አሳልፋችሁ ልትሰጡኝ ከሆነ፣ የአባቶቻችን አምላክ ይመልከተው፤ ይፍረደውም።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ዳዊትም ወደ እነርሱ ቀርቦ እንዲህ አላቸው፤ “ወደዚህ የመጣችሁት በወዳጅነት ልትረዱኝ ከሆነ መልካም ነው፤ በደስታ እቀበላችኋለሁ፤ ከእኛም ጋር ሁኑ! እኔ ምንም ሳላደርጋችሁ ለጠላቶቼ አሳልፋችሁ ልትሰጡኝ ከሆነ ግን የቀድሞ አባቶቻችን አምላክ ተመልክቶ ይፍረደው።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ዳዊ​ትም ሊገ​ና​ኛ​ቸው ወጥቶ፥ “በሰ​ላም ወደ እኔ መጥ​ታ​ችሁ እንደ ሆነ ልቤ ከእ​ና​ንተ ጋር አንድ ይሆ​ናል፤ ለጠ​ላ​ቶቼ አሳ​ል​ፋ​ችሁ ልት​ሰ​ጡኝ መጥ​ታ​ችሁ እንደ ሆነ ግን፥ በእጄ ዓመፅ የለ​ብ​ኝ​ምና የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ ይመ​ል​ከ​ተው፥ ይፍ​ረ​ደ​ውም፤” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ዳዊትም ሊገናኛቸው ወጥቶ “ትረዱኝ ዘንድ በሰላም ወደ እኔ መጥታችሁ እንደ ሆነ ልቤ ከእንናተ ጋር አንድ ይሆናል፤ ለጠላቶቼ አሳልፋችሁ ልትሰጡኝ መጥታችሁ እንደ ሆነ ግን፥ በእጄ አመፅ የለብኝምና የአባቶቻችን አምላክ ይመልከተው፤ ይፍረደውም፤” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 12:17
24 Referencias Cruzadas  

የአባቴ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ፍርሃት፥ ከእኔ ጋር ባይሆን ኖሮ፥ ዛሬ ባዶ እጄን በሰደድኸኝ ነበር፥ እግዚአብሔር መከራዬንና የእጆቼን ልፋት አየ፥ ትናንትና ሌሊትም ገሠጸህ።”


የአብርሃም አምላክ የናኮርም አምላክ፥ የአባታቸውም አምላክ፥ በእኛ መካከል ይፍረድ።” ያዕቆብም በአባቱ በይስሐቅ ፍርሃት ማለ።


የሐጊት ልጅ አዶንያስ ወደ ሰሎሞን እናት ወደ ቤርሳቤህ ሄደ፤ ቤርሳቤህም “ወደ እኔ የመጣኸው በሰላም ነውን?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም “አዎን በሰላም ነው የመጣሁት” ሲል መለሰ።


ኢዩ ተነሥቶ እንደገና ጉዞ ቀጠለ፤ በመንገድ ሳለም የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን አገኘ፤ ኢዩም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ “እኔና አንተ በሐሳብ አንድ ነን፤ ታዲያ ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮናዳብም “አዎ እተባበርሃለሁ” ሲል መለሰ። ኢዩም “እንግዲያውስ ጨብጠኝ” ሲል መለሰለት፤ እጅ ለእጅ ተያይዘው ኢዩ ደግፎት በሠረገላው ላይ አስቀመጠውና፥


ኢዮራምም “ኢዩ ሆይ፥ አመጣጥህ በሰላም ነውን?” ሲል ጠየቀ። ኢዩም፦ “እናትህ ኤልዛቤል ባመጣችው አስማትና የጣዖት አምልኮ ውስጥ ተነክረን እስካለን ድረስ ምን ሰላም አለ?” ሲል መለሰለት።


ዳዊትም ወደ ነበረባት ወደ አምባይቱ ከብንያምና ከይሁዳ ወገን ሰዎች መጡ።


መንፈስም በሠላሳው አለቃ በዓማሣይ ላይ ወረደ፥ እርሱም እንዲህ አለ፦ “ዳዊት ሆይ! እኛ የአንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ! እኛ ከአንተ ጋር ነን፤ አምላክህ ይረዳሃልና ሰላም ሰላም ለአንተ ይሁን፥ ለሚረዱህም ሰላም ይሁን።” ዳዊትም ተቀበላቸው፥ የጭፍራም አለቆች አደረጋቸው።


ጠላት ነፍሴን ያሳድዳት ያግኛትም፥ ሕይወቴንም በምድር ላይ ይርገጣት፥ ክብሬንም በትቢያ ላይ ያዋርዳት።


አቤቱ፥ መንገድህን ምራኝ፥ በእውነትህም እሄዳለሁ፥ ስምህን ለመፍራት ልቤ ደስ ይለዋል።


እኔን ለዘለዓለም በመፍራት ለእነርሱም ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው መልካም እንዲሆንላቸው አንድ ልብና አንድ መንገድ እሰጣቸዋለሁ።


ጌታም ሰይጣንን፦ “ሰይጣን ሆይ፥ ጌታ ይገሥጽህ፤ ኢየሩሳሌምን የመረጠ ጌታ ይገሥጽህ! በውኑ ይህ ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይደለምን?” አለው።


ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፤ ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበረ እንጂ ካለው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደሆነ ማንም አልተናገረም።


ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! ሁላችሁ ተስማምታችሁ በአንድ ልቡና እና በአንድ አቋም በአንድነት የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ።


በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! ደኅና ሁኑ። ፍጹማን ሁኑ፤ ምክሬን ስሙ፤ በአንድ ልብ ሁኑ፤ በሰላም ኑሩ፤ የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።


ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ብቻ ኑሩ፤ በዚህም መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ፥ በአንድ ልብ ስለ ወንጌል እምነት አብራችሁ መጋደላችሁንና በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ መቆማችሁን እሰማለሁ።


ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤


ነገር ግን የመላእክት አለቃ ሚካኤል ስለ ሙሴ ሥጋ ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ሲናገር “ጌታ ይገሥጽህ!” አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊያመጣበት አልደፈረም።


ሳሙኤል ጌታ ያለውን ነገር አደረገ። ቤተልሔም እንደደረሰም፥ የከተማዪቱ ሽማግሌዎች እየተንቀጠቀጡ ሊገናኙት መጡ፥ እነርሱም “አመጣጥህ ለሰላም ነውን?” ብለው ጠየቁት።


ዳዊት ከሳኦል ጋር የሚያደርገውን ንግግር እንዳበቃ፤ የዮናታን ነፍስ ከዳዊት ነፍስ ጋር ተቆራኘች፤ እንደራሱም አድርጎ ወደደው።


ዮናታን እንደ ራሱ አድርጎ ስለ ወደደው ከዳዊት ጋር ኪዳን አደረገ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos