Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 4:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እርሱንና ዕቃዎቹን ሁሉ በአቆስጣ ቁርበት መሸፈኛ ውስጥ ያድርጉ፥ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከዚያም ይህንና ከዚሁ ጋራ የተያያዙትን ዕቃዎች ሁሉ በአቆስጣ ቍርበት መሸፈኛ ጠቅልለው በመሸከሚያ ሳንቃ ላይ ያስቀምጡት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 መቅረዙንና የመገልገያ ዕቃዎቹን ሁሉ በአቆስጣ ቁርበት መሸፈኛ ውስጥ ያኑሩት፥ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 መቅረዙንና የእርሱን መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ በቈዳ መሸፈኛ ጠቅልለው በመሸከሚያ ተራዳ ላይ ያኑሩት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እር​ስ​ዋ​ንና ዕቃ​ዎ​ች​ዋን ሁሉ በአ​ቆ​ስጣ ቍር​በት መሸ​ፈኛ ውስጥ ያድ​ርጉ፤ በመ​ሸ​ከ​ሚ​ያ​ውም ላይ ያድ​ር​ጉት።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 4:10
6 Referencias Cruzadas  

መቅረዝንም ከጥሩ ወርቅ አድርግ፤ መቅረዙ ከእግሩና ከአገዳው ጋር በተቀጠቀጠ ሥራ ይደረግ፤ ጽዋዎቹም ጕብጕቦቹም አበቦቹም አንድነት በእርሱ ይደረጉበት።


የፍየልም ጠጉር፥ ቀይ የአውራ በግ ቁርበት፥ የአስቆጣ ቁርበት፥ የግራርም እንጨት፥


በወርቁም መሠዊያ ላይ ሰማያዊውን መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፥ በአቆስጣም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።


በመቅደስም ውስጥ የሚያገልግሉበትን የማገልገያውን ዕቃ ሁሉ ይውሰዱ፥ በሰማያዊውም መጐናጸፊያ ውስጥ ያስቀምጡት፥ በአቆስጣም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት፥ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉት።


በላዩም የአስቆጣውን ቁርበት መሸፈኛ ያድርጉበት፥ ከእርሱም በላይ ሁለንተናው ሰማያዊ የሆነ መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።


ሰማያዊውንም መጐናጸፊያ ይውሰዱ፥ የሚያበራውንም መቅረዝ፥ ቀንዲሎቹንም፥ መኰስተሪያዎቹንም፥ የኩስታሪ ማድረጊያዎቹንም፥ እርሱንም ለማገልገል የዘይቱን ዕቃዎች ሁሉ ይሸፍኑ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos