Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 32:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የሮቤልና የጋድ ልጆችም እጅግ ብዙ እንስሶች ነበሩአቸው፤ እነሆም፥ የኢያዜር ምድርና የገለዓድ ምድር ለእንስሶች የተመቸ ስፍራ እንደ ነበረ ባዩ ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እጅግ ብዙ የሆነ የቀንድ ከብት፣ የበግና የፍየል መንጋዎች የነበሯቸው የሮቤልና የጋድ ነገዶች የኢያዜርና የገለዓድ ምድር ለከብት ምቹ ስፍራዎች መሆናቸውን አዩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የሮቤልና የጋድ ልጆችም እጅግ ብዙ እንስሶች ነበሩአቸው፤ እነሆም፥ የኢያዜር ምድርና የገለዓድ ምድር ለእንስሶች የተመቸ ስፍራ እንደ ነበረ ባዩ ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የሮቤልና የጋድ ነገዶች እጅግ ብዙ የከብት መንጋ ነበራቸው፤ የያዕዜርና የገለዓድ ምድር ለከብት ተስማሚ መሆኑን ባዩ ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ለሮ​ቤል ልጆ​ችና ለጋድ ልጆች እጅግ ብዙ እን​ስ​ሶች ነበ​ሩ​አ​ቸው፤ እነ​ሆም፥ የኢ​ያ​ዜር ምድ​ርና የገ​ለ​ዓድ ምድር የከ​ብት ሀገር እንደ ነበረ አዩ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 32:1
30 Referencias Cruzadas  

ሙሴም ሰላዮችን ወደ ኢያዜር ሰደደ፤ መንደሮችዋንም ወሰዱ፥ በዚያም የነበሩትን አሞራውያን አባረሩ።


ዓጥሮትሽፋንን፥ ኢያዜርን፥ ዮግብሃን፥


እግዚአብሔር በእስራኤል ማኅበር ፊት የመታው ምድር፥ አጣሮት፥ ዲቦን፥ ኢያዜር፥ ነምራ፥ ሐሴቦን፥ ኤልያሊ፥ ሴባማ፥ ናባው፥ ባያን፥ ለእንስሶች የተመቸ ምድር ነው፤ ለእኛም ለባሪያዎችህ እንስሶች አሉን።


በቀርሜሎስ መካከል ባለው ዱር ብቻቸውን የተቀመጡት ሰዎችህ፥ የርስትህን በጎች፥ በበትርህ አግድ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።


እስራኤልንም ወደ ማሰማርያው እመልሳለሁ፥ በቀርሜሎስና በባሳንም ላይ ይሰማራል፥ ሰውነቱም በኤፍሬም ተራራና በገለዓድ ላይ ትጠግባለች።


ዮርዳኖስንም ተሻገሩ፥ በጋድ ሸለቆ መካከል ባለችው በኢያዜር ከተማ ቀኝ በኩል በአሮዔር ላይ ሰፈሩ።


ድንበራቸውም ኢያዜርና የገለዓድ ከተሞች ሁሉ፥ የአሞንም ልጆች ምድር እኩሌታ በረባት ፊት እስካለችው እስከ አሮዔር ድረስ፥


ልጆቻችን፥ ሚስቶቻችንም፥ መንጎቻችንም፥ እንስሶቻችንም ሁሉ በዚያ በገለዓድ ከተሞች ይሆናሉ፤


ደግሞም ሌላ ብዙ ድብልቅ ሕዝብ መንጎችና ላሞችም እጅግ ብዙም ከብቶች ከእነርሱ ጋር ወጡ።


ፈርዖንንም እንዲህ አሉት፦ በምድር ልንቀመጥ በእንግድነት መጣን የባርያዎችህ በጎች የሚስማሩበት ስፍራ የለምና ራብ በከነዓን ምድር እጅግ ጸንቶቸልና አሁንም ባርያዎችህ በጌሤም ምድር እንድንቀመጥ እንለምንሃለን።


ልያም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች ስሙም ሮቤል ብላ ጠራችው እግዚአብሔር መከራዬን አይቶአልና፥ እንግዲህም ወዲህ ባሌ ይወድደኛል ብላለችና።


ከአብራም ጋር የሄደው ሎጥ ደግሞ የላምና የበግ መንጋ ድንኳንም ነበረው።


አብራምም በከብት በብርና በወርቅ እጅግ በለጠገ።


የጋድና የሮቤል ልጆች መጥተው ሙሴንና ካሁኑን አልዓዛርን የማኅበሩንም አለቆች እንዲህ ብለው ተናገሩአቸው፦


በዚያ የአለቃ እድል ፈንታ ቀርቶአልና 2 የመጀመሪያውን ክፍል ለራሱ መረጠ፤ 2 ወደ ሕዝብ አለቆችም መጣ፤ 2 የእግዚአብሔርንም ጽድቅ፥ 2 ፍርዱንም ከእስራኤል ጋር አደረገ።


የሮቤልም ልጆች የጋድም ልጆች የምናሴም ነገድ እኩሌታ ሄዱ፥ በሙሴም እጅ በተሰጠ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ተቀበሉአት ወደ ርስታቸው ወደ ገለዓድ ምድር ይገቡ ዘንድ በከነዓን ምድር ካለችው ከሴሎ ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ተመለሱ።


መንጎች ሲያፍዋጩ ለመስማት በበጎች ጉረኖ መካከል ለምን ተቀመጥህ? በሮቤል ፈሳሾች አጠገብ ታላቅ የልብ ምርምር ነበረ።


እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ቤት እንዲህ ይላልና፦ አንተ በእኔ ዘንድ እንደ ገለዓድና እንደ ሊባኖስ ራስ ነህ፥ ነገር ግን በእርግጥ ምድረ በዳ ማንም የማይቀመጥባቸውም ከተሞች አደርግሃለሁ።


የእስራኤልም ልጆች በገለዓድ ምድር ወዳሉት ወደ ሮቤል ልጆችና ወደ ጋድ ልጆች ወደ ምናሴም ነገድ እኩሌታ የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን ላኩ።


ወደ ገለዓድም ወደ ተባሶን አዳሰይ አገር መጡ፥ ወደ ዳንየዓንም ደረሱ፥ ወደ ሲዶናም ዞሩ፥


እነዚህም በስማቸው የተጻፉ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን መጥተው ድንኳኖቻቸውንና በዚያ የተገኙትን ምዑናውያንን መቱ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ በዚያም ለመንጎቻቸው መሰማርያ ነበረና በስፍራቸው ተቀመጡ።


በገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለምን? የወገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አልሆነም?


አንቺ የሴባማ ወይን ሆይ፥ ከኢያዜር ልቅሶ ይልቅ ለአንቺ አለቅሳለሁ፥ ቅርንጫፎችሽ ባሕርን ተሻግረዋል፥ ወደ ኢያዜርም ባሕር ደርሰዋል፥ አጥፊው በሰብልሽና በወይንሽ ላይ መጥቶአል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios