Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 3:12 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እነሆ፥ እኔ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ማኅፀን በሚከፍተው በበኵሩ ሁሉ ፋንታ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ወስጄአለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “እነሆ፤ በኵር ሆኖ በሚወለደው ሁሉ ምትክ ሌዋውያኑን ከእስራኤላውያን ወስጃለሁ፤ ስለዚህ ሌዋውያን የእኔ ናቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 “እነሆ፥ እኔ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ማኅፀን በሚከፍተው በበኩሩ ሁሉ ፋንታ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ወስጄአለሁ፤ ሌዋውያንም የእኔ ናቸው፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12-13 “እነሆ ሌዋውያን የእኔ አገልጋዮች ናቸው፤ የግብጻውያንን በኲር ሁሉ በገደልኩ ጊዜ ከያንዳንዱ እስራኤላዊ የሚወለደውን በኲርና ከእንስሶቹም በኲር የሆነውን ሁሉ ለእኔ የተለየ እንዲሆን አድርጌ ነበር፤ አሁን ግን በኲር ሆነው የሚወለዱትን ወንዶች ልጆች የራሴ በማድረግ ፈንታ ሌዋውያንን መርጬአለሁ፤ እነርሱ የእኔ አገልጋዮች ይሆናሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 “እነሆ፥ እኔ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ መጀ​መ​ሪያ በሚ​ወ​ለ​ደው በበ​ኵር ሁሉ ፋንታ ሌዋ​ው​ያ​ንን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለይች ወስ​ጃ​ለሁ፤ በእ​ነ​ርሱ ፋንታ ሌዋ​ው​ያን ለእኔ ይሁኑ፤

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 3:12
8 Referencias Cruzadas  

እነርሱም ከእስራኤል ልጆች መካከል ፈጽሞ ለእኔ ተሰጥተዋልና፤ በእስራኤል ልጆች በኵራት ሁሉ፥ ማኅፀን በሚከፍት ሁሉ ፋንታ ለእኔ ወስጄአቸዋለሁ።


ሌዋውያንንም በእስራኤል ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ፥ የሌዋውያንንም እንስሶች በእስራኤል ልጆች እንስሶች በኵር ሁሉ ፋንታ ለእኔ ለእግዚአብሔር ውሰድ አለው።


እኔም፥ እነሆ፥ ሌዋውያንን ወንድሞቻችሁን ከእስራኤል ልጆች መካከል ወስጄአለሁ፤ የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ያደርጉ ዘንድ ለእግዚአብሔር የተሰጡ ለእናንተ ስጦታ ናቸው።


በእስራኤልም ልጆች በኵራት ሁሉ ፋንታ ሌዋውያንን ወስጄአለሁ።


ሌዋውያንን በእስራኤል ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ፥ የሌዋውያንንም እንስሶች በእንስሶቻቸው ፋንታ ውሰድ፤ ሌዋውያንም ለእኔ ይሁኑ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


“በእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም ከእንስሳም ማሕፀንን የሚከፍት በኵርን ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ፤ የእኔ ነው።”


እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


እንዲሁ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይ፤ ሌዋውያንም ለእኔ ይሁኑ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios