Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 25:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እስራኤልም ብዔልፌጎርን ተከተለ፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ስለዚህ እስራኤል በኣል ፌጎርን በማምለክ ተባበረ፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ በላዩ ነደደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እስራኤልም ብዔልፌጎርን ተከተለ፤ የጌታም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በዚህም ዐይነት እስራኤላውያን በፔዖር ለባዓል ጣዖት በመስገዳቸው እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ተቈጣ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እስ​ራ​ኤ​ልም ለብ​ዔል ፌጎር ራሳ​ቸ​ውን ለዩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 25:3
13 Referencias Cruzadas  

አንተም የሰጠሁህን ርስት ትለቅቃለህ ለዘላለምም በማታውቃትም ምድር ለጠላቶቻችሁ ባሪያ አደርግሃለሁ፥ ለዘላለም የሚነድደውን እሳት በቍጣዬ አንድዳችኋልና።


ወንዶችም ደግሞ ከጋለሞቶች ጋር ይጫወታሉና፥ ከጋለሞቶችም ጋር ይሠዋሉና ሴቶች ልጆቻችሁ በገለሞቱ ጊዜ፥ ሙሽሮቻችሁም ባመነዘሩ ጊዜ አልቀጣቸውም፥ የማያስተውልም ሕዝብ ይገለበጣል።


እስራኤልን በምድረ በዳ እንዳለ ወይን ሆኖ አገኘሁት፥ አባቶቻችሁንም ከመጀመሪያዋ ዓመት እንደ በለስ በኵራት ሆነው አየኋቸው፥ እነርሱ ግን ወደ ብዔልፌጎር መጡ፥ ለነውርም ተለዩ፥ እንደ ወደዱትም ርኩስ ሆኑ፥


ሙሴም የእስራኤልን ዳኞች፦ እናንተ ሁሉ ብዔልፌጎርን የተከተሉትን ሰዎቻችሁን ግደሉ አላቸው።


እነሆ፥ እነዚህ በፌጎር ምክንያት በበለዓም ምክር እግዚአብሔርን ይበድሉ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ዕንቅፋት ሆኑ፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ሆነ።


እኛ እስከ ዛሬ ድረስ ከእርሱ ያልነጻንበት የፌጎር ኃጢአት ጥቂት ነውን? በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሰፍት ወረደ።


የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነ ነገር አደረጉ፥ በኣሊምንም አመለኩ።


እግዚአብሔርንም ትተው በኣልንና አስታሮትን አመለኩ።


የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ ወደ ማረኩአቸውም ማራኪዎች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ በዙሪያቸውም ባሉት በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ ጠላቶቻቸውንም ከዚያ ወዲያ ሊቋቋሙ አልቻሉም።


የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ እንዲህም አለ፦ ይህ ሕዝብ ለአባቶቻቸው ያዘዝሁትን ቃል ኪዳን ስለ ተላለፉ፥ ድምፄንም ስላልሰሙ አባቶቻቸውም እንደ ጠበቁ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos