ዘኍል 21:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ሕዝቡም በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ፦ በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣችሁን? እንጀራ የለም፥ ውኃ የለም፤ ሰውነታችንም ይህን ቀላል እንጀራ ተጸየፈ ብለው ተናገሩ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 በእግዚአብሔርና በሙሴም ላይ ተነሥተው፣ “በምድረ በዳ እንድንሞት ከግብጽ ያወጣችሁን ለምንድን ነው? ምግብ የለ! ውሃ የለ! ይህን የማይረባ ምግብ ሰውነታችን ተጸይፎታል” ሲሉ ተናገሩ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ሕዝቡም በጌታና በሙሴ ላይ እንዲህ ብለው ተናገሩ፦ “በምድረ በዳ እንድንሞት ከግብጽ ለምን አወጣችሁን? እንጀራ የለም፥ ውኃም የለም፤ ሰውነታችንም ይህን የሚያንገሸግሽ እንጀራ ተጸየፈ።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 በእግዚአብሔርና በሙሴም ላይ ክፉ ቃል በመናገር እንዲህ ሲሉ አጒረመረሙ፤ “ምግብና ውሃ በሌለበት በዚህ በረሓ እንሞት ዘንድ ከግብጽ ምድር ለምን አወጣችሁን? ይህን አስከፊ ምግብ ሰውነታችን ተጸይፎታል!” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ሕዝቡም፥ “በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣኸን?” ብለው እግዚአብሔርንና ሙሴንም አሙ። “እንጀራ የለም፤ ውኃም የለምና፥ ሰውነታችንም ይህን ጥቅም የሌለው እንጀራ ተጸየፈች” ብለው ተናገሩ። Ver Capítulo |