Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 2:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በምሥራቅ በኩል ወደ ፀሐይ መውጫ የሚሰፍሩት እንደ ሠራዊቶቻቸው የይሁዳ ሰፈር ዓላማ ሰዎች ይሆናሉ፤ የይሁዳ ልጆችም አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በምሥራቅ በኩል በፀሓይ መውጫ፤ የይሁዳ ምድብ፤ በየሰራዊቱና በዐርማቸው ሥር ይስፈር፤ የይሁዳ ሕዝብ አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በምሥራቅ በኩል ወደ ፀሐይ መውጫ የሚሰፍሩት እንደ ሠራዊቶቻቸው የይሁዳን ሰፈር ዓላማ የያዙት ይሆናሉ፤ የይሁዳ ልጆችም አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ፀሐይ በሚወጣበት በስተምሥራቅ በኩል የሚሰፍሩት በይሁዳ ሥር የተመደቡት ነገዶች ናቸው። የይሁዳ ነገድ መሪም የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በመ​ጀ​መ​ሪያ በም​ሥ​ራቅ በኩል የሚ​ሰ​ፍ​ሩት ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር የይ​ሁዳ ሰፈር ሰዎች ይሆ​ናሉ፤ የይ​ሁዳ ልጆ​ችም አለቃ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 2:3
19 Referencias Cruzadas  

አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም የይሁዳን ልጆች አለቃ ነአሶንን ወለደ፤


አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤


ከይሁዳ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን፥


ኤስሮምም አራምን ወለደ፤ አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤


ይሁዳም በወንድሞቹ መካከል በረታ፤ አለቃም ከእርሱ ሆነ፤ ብኵርናው ግን ለዮሴፍ ነበረ።


አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነበረ፤ የአሚናዳብ ልጅ የነአሶን መባ ይህ ነበረ።


በመጀመሪያውም ቀን መባውን ያቀረበ ከይሁዳ ነገድ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ።


አሮንም የአሚናዳብን የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፤ እርስዋም ዮናዳብንና አብድን አልዓዛርንና ኢታምርን ወለደችለት።


ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።


በማደሪያውም ፊት በምሥራቅ በኩል በመገናኛው ድንኳን ፊት በስተ ፀሐይ መውጫ የሚሰፍሩት ሙሴና አሮን ልጆቹም ይሆናሉ፥ መቅደሱንም ለእስራኤል ልጆች ይጠብቃሉ፤ ልዩም ሰው ቢቀርብ ይገደል።


እስራኤልም በዚያች አገር በተቀመጠ ጊዜ ሮቤል ሄደ የአባቱንም ቁባት ባላን ተገናኛት እስራኤልም ሰማ።


የያዕቆብም ልጆች አሥራ ሁለት ናቸው የልያ ልጆች የያዕቆብ በኵር ልጅ ሮቤል ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፤


ከእናንተም ጋር የሚቆሙት ሰዎች ስሞቻቸው እነዚህ ናቸው፤ ከሮቤል የሰዲዮር ልጅ


መለከትንም ከፍ ባለ ድምፅ ስትነፉ በምሥራቅ በኩል የሰፈሩት ይጓዙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios