Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 16:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ለቆሬም ለወገኑም ሁሉ፦ ነገ እግዚአብሔር ለእርሱ የሚሆነውን፥ ቅዱስም የሚሆነውን ያስታውቃል፤ የመረጠውንም ሰው ወደ እርሱ ያቀርበዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ቆሬንና ተከታዮቹን በሙሉ እንዲህ አላቸው፤ “የርሱ የሆነውና የተቀደሰው ማን መሆኑን እግዚአብሔር ጧት ያሳውቃል፤ ወደ ራሱም ያመጣዋል፤ የሚመርጠውን ሰው ወደ ራሱ እንዲቀርብ ያደርገዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ለቆሬም እርሱንም ለተከሉት ሁሉ እንዲህ ቡሎ ተናገረ፦ “ነገ ጠዋት ጌታ ለእርሱ የሆነውን ሰው፥ ቅዱስም ማን እንሆነ፥ ወደ እርሱም ለመቅረብ የተፈቀደለትን ሰው ያሳውቃል፤ የመረጠውንም ሰው ወደ እርሱ እንዲቀርብ ይፈቅድለታል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ቆሬንና ተከታዮቹን እንዲህ አላቸው፦ “ነገ ጠዋት እግዚአብሔር ለእርሱ የተለየ ማን እንደ ሆነ ለይቶ ያሳየናል፤ ይኸውም የእርሱ የሆነውንና የመረጠውን በመሠዊያው ላይ ያገለግለው ዘንድ ወደ እርሱ እንዲቀርብ ይፈቅድለታል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ለቆ​ሬም ለማ​ኅ​በ​ሩም ሁሉ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ነገ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ርሱ የሚ​ሆ​ኑ​ትን፥ ቅዱ​ሳ​ንም የሆ​ኑ​ትን ያያል፥ ያው​ቃ​ልም፤ የመ​ረ​ጣ​ቸ​ው​ንም ሰዎች ወደ እርሱ ያቀ​ር​ባ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 16:5
38 Referencias Cruzadas  

እንዲህም ይሆናል፤ የመረጥሁት ሰው በትር ታቈጠቍጣለች፥ በእናንተም ላይ የሚያጕረመርሙባችሁን የእስራኤልን ልጆች ማጕረምረም ከእኔ ዘንድ አጠፋለሁ።


ሙሴም አሮንን፦ እግዚአብሔር፦ ወደ እኔ በሚቀርቡ እቀደሳለሁ፥ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ ብሎ የተናገረው ይህ ነው አለው፤ አሮንም ዝም አለ።


ሆኖም፦ ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፥ ደግሞም፦ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዓመፅ ይራቅ የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።


በሙሴና በአሮን ላይ ተሰብስበው፦ ማኅበሩ ሁሉ እያንዳንዳቸው ቅዱሳን ናቸውና፥ እግዚአብሔርም በመካከላቸው ነውና እናንተ እጅግ አብዝታችኋል፤ በእግዚአብሔርም ጉባኤ ላይ ለምን ትታበያላችሁ? አሉ።


መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።


እርሱም አለኝ፦ የአባቶቻችን አምላክ ፈቃዱን ታውቅ ዘንድና ጻድቁን ታይ ዘንድ ከአፉም ድምፅን ትሰማ ዘንድ አስቀድሞ መርጦሃል


እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ፦ “በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ” አለ።


ሲጸልዩም፦ “የሁሉን ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ፥ ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ስፍራ ይሄድ ዘንድ በተዋት በዚህች አገልግሎትና ሐዋርያነት ስፍራን እንዲቀበል የመረጥኸውን ከእነዚህ ከሁለቱ አንዱን ሹመው አሉ።”


እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ።


ተመልሳችሁም በጻድቁና በኃጢአተኛው መካከል፥ ለእግዚአብሔር በሚገዛውና በማይገዛው መካከል ትለያላችሁ።


ወደ ሰሜንም የሚመለከተው ቤት መሠዊያውን ለማገልገል ለሚተጉ ካህናት ነው፥ እነዚህ ከሌዊ ልጆች መካከል ያገለግሉት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ የሳዶቅ ልጆች ናቸው አለኝ።


ከእስራኤልም ነገድ ሁሉ ካህን ይሆነኝ ዘንድ፥ በመሠዊያዬ ላይ ይሠዋ ዘንድ፥ ዕጣንንም ያጥን ዘንድ ኤፋድንም በፊቴ ይለብስ ዘንድ ለእኔ መረጥሁት፥ የእስራኤልንም ልጆች የእሳት ቍርባን ሁሉ ስለ ምግብ ለአባትህ ቤት ሰጠሁ።


አንተም ወንድምህን አሮንን ከእርሱም ጋር ልጆቹን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይተህ ካህናት ይሆኑልኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅርብ፤ አሮንን የአሮንንም ልጆች፥ ናዳብን አብዩድንም አልዓዛርንም ኢታምርንም፥ አቅርብ።


ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።


አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።


ከብዙ ክርክርም በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው ወንድሞች ሆይ፥ አሕዛብ ከአፌ የወንጌልን ቃል ሰምተው ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር በመጀመሪያው ዘመን ከእናንተ እኔን እንደ መረጠኝ እናንተ ታውቃላችሁ።


አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን፥ ልብሱንም፥ የቅብዓቱንም ዘይት፥ ለኃጢአት መሥዋዕትም የሆነውን ወይፈን፥ ሁለቱንም አውራ በጎች፥ የቂጣውንም እንጀራ ሌማት ውሰድ፤


ኃጢአትም እንዳይሆንባቸው እንዳይሞቱም፥ ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ በመቅደሱም ያገለግሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናል፤ ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘላለም ሥርዓት ይሆናል።


እንዲሁ አድርጉ፤ ቆሬና ወገንህ ሁሉ፥ ጥናዎቹን ውሰዱ፤


እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነች የአሮን በትር አቈጠቈጠች፥ ለመለመችም፥ አበባም አወጣች፥ የበሰለ ለውዝም አፈራች።


አለቃቸው ከእነርሱ ውስጥ ይሆናል፥ ገዥአቸውም ከመካከላቸው ይወጣል፥ እኔ አቀርበዋለሁ እርሱም ይቀርባል፥ ይህስ ባይሆን ወደ እኔ ለመቅረብ የሚደፍር ማን ነው? ይላል እግዚአብሔር።


እነሆ፥ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና በጠነከረው አምባ ላይ ከዮርዳኖስ ትዕቢት ውስጥ እንደ አንበሳ ይወጣል፥ የተመረጠውንም በእርስዋ ላይ እሾመዋለሁ፥ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜ የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቃወም እረኛ ማን ነው?


እነሆ፥ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና በጠነከረው አምባ ላይ ከዮርዳኖስ ትዕቢት ውስጥ እንደ አንበሳ ይወጣል፥ የተመረጠውንም በእርስዋ ላይ እሾመዋለሁ፥ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜ የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቃወም እረኛ ማን ነው?


ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ለሚቀርቡ ከሳዶቅ ዘር ለሚሆኑ ለሌዋውያኑ ካህናት ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትሰጣቸዋለህ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ከምድርም የተቀደሰ የዕጣ ክፍል ይሆናል፥ እግዚአብሔርን ያገለግሉ ዘንድ ለሚቀርቡ ለመቅደሱ አገልጋዮች ለካህናቱ ይሆናል፥ ለቤቶቻቸውም የሚሆን ስፍራ ለመቅደስም የሚሆን የተቀደሰ ስፍራ ይሆናል።


ይህንም ሁሉ ወንድምህን አሮንን ከእርሱም ጋር ልጆቹን ታለብሳቸዋለህ፤ በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀባቸዋለህ፥ ትክናቸዋለህ፥ ትቀድሳቸውማለህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios