Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 16:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ስለዚህም አንተና ወገንህ ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ተሰብስባችኋል፤ በእርሱም ላይ ታጉረመርሙ ዘንድ አሮን ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 አንተና ተከታዮችህ ሁሉ አባሪ ተባባሪ ሆናችሁ የተነሣችሁት በእግዚአብሔር ላይ ነው፤ ለመሆኑ ታጕረመርሙበት ዘንድ አሮን ማነው?”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ስለዚህም አንተና አንተንም የሚከተሉህ ሁሉ በጌታ ላይ ተሰብስባችኋል፤ በእርሱም ላይ የምታጉረመርሙት አሮን ማን ስለ ሆነ ነው?”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ስለዚህ አንተና ተባባሪዎችህ የተሰበሰባችሁት በእግዚአብሔር ላይ ነው፤ በአሮን ላይ የምታጒረመርሙት እርሱ ማን ነው?”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ስለ​ዚ​ህም አን​ተና ማኅ​በ​ርህ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ተሰ​ብ​ስ​ባ​ች​ኋል፤ በእ​ር​ሱም ላይ ታጕ​ረ​መ​ርሙ ዘንድ አሮን ማን​ነው?”

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 16:11
15 Referencias Cruzadas  

ከቆሬና ከሜራሪ ልጆች የነበሩ የበረኞች ሰሞን ይህ ነበረ።


ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፦ የምንጠጣውን ውኃ ስጠን አሉት። ሙሴም፦ ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተናላችሁ? አላቸው።


ሕዝቡም ክፉ ሆነው በእግዚአብሔር ላይ አጉረመረሙ፤ እግዚአብሔርም ሰምቶ ተቈጣ፤ የእግዚአብሔርም እሳት በመካከላቸው ነደደች፥ የሰፈሩንም ዳር በላች።


ሙሴም የኤልያብን ልጆች ዳታንና አቤሮንን እንዲጠሩአቸው ላከ፤ እነርሱም፦ አንመጣም፤


በሙሴና በአሮን ላይ ተሰብስበው፦ ማኅበሩ ሁሉ እያንዳንዳቸው ቅዱሳን ናቸውና፥ እግዚአብሔርም በመካከላቸው ነውና እናንተ እጅግ አብዝታችኋል፤ በእግዚአብሔርም ጉባኤ ላይ ለምን ትታበያላችሁ? አሉ።


የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል፥ እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል።


እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ማናቸውንም የምልከውን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።”


ሳትሸጠው የአንተ አልነበረምን? ከሸጥኸውስ በኋላ በሥልጣንህ አልነበረምን? ይህን ነገር ስለ ምን በልብህ አሰብህ? እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሸህም” አለው።


ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ።


ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታንጕኦርጕሩ።


አጵሎስ እንግዲህ ምንድር ነው? ጳውሎስስ ምንድር ነው? በእነርሱ እጅ ያመናችሁ አገልጋዮች ናቸው፤ ለእያንዳንዳቸውም ጌታ እንደ ሰጣቸው ያገለግላሉ።


እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፥ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል።


እግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው፦ በእነርሱ ላይ እንዳልነግሥ እኔን እንጂ አንተን አልናቁምና በሚሉህ ነገር ሁሉ የሕዝቡን ቃል ስማ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos