Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 11:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ሕዝቡም ወደ ሙሴ ጮኹ፤ ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እሳቲቱም ጠፋች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ሕዝቡ ወደ ሙሴ ጮኸ፤ ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እሳቲቱም ጠፋች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሕዝቡም ወደ ሙሴ ጮኹ፤ ሙሴም ወደ ጌታ ጸለየ፥ እሳቱም ጠፋ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ሕዝቡም ያማልዳቸው ዘንድ ወደ ሙሴ ጮኹ፤ ሙሴም እግዚአብሔርን ለመነ፤ እሳቱም ተገታ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሕዝ​ቡም ወደ ሙሴ ጮኹ፤ ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ፤ እሳ​ቲ​ቱም ጠፋች።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 11:2
23 Referencias Cruzadas  

ሕዝቡም ወደ ሙሴ መጥተው፦ በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ስለ ተናገርን በድለናል፤ እባቦችን ከእኛ ያርቅልን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን አሉት።


እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።


ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ ሞትም የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም።


ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባልና፤


ሲሞንም መልሶ፦ “ካላችሁት አንዳች እንዳይደርስብኝ እናንተው ወደ ጌታ ለምኑልኝ” አላቸው።


ነብዩንም ኤርምያስን፦ ዓይኖችህ እንዳዩን ከብዙ ጥቂት ቀርተናልና ልመናችን፥ እባክህ፥ በፊትህ ትድረስ፥ አምላክህም እግዚአብሔር የምንሄድበትን መንገድና የምናደርገውን ነገር ያሳየን ዘንድ ስለ እኛ፥ ስለዚህ ቅሬታ ሁሉ፥ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ አሉት።


ንጉሡም ሴዴቅያስ፦ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ስለ እኛ ጸልይ ብሎ የሰሌምያን ልጅ ዮካልንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ ላከ።


እግዚአብሔርም እንደዚህ አለኝ፦ ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አይዘነብልም፥ ከፊቴ ጣላቸው፥ ይውጡ።


ምናልባት በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ ጌታው የአሦር ንጉሥ የላከውን የራፋስቂስን ቃል አምላክህ እግዚአብሔር ይሰማ እንደ ሆነ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም ስለ ሰማው ቃል ይገሥጸው እንደ ሆነ፥ ስለዚህ ለቀረው ቅሬታ ጸልይ አሉት።


አቤቱ በፊትህስ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ ይህ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነውና ጌታዬ በመካከላችን ይሂድ፤ ጠማማነታችንንና ኃጢአታችንንም ይቅር በለን፥ ለርስትህም ተቀበለን አለ።


አሮንም ሙሴን፦ ጌታዬ ሆይ፥ ስንፍና አድርገናልና፥ በድለንማልና እባክህ፥ ኃጢአት አታድርግብን።


ሙሴም ወደ እግዚአብሔር እየጮኸ፦ አቤቱ፥ እባክህ፥ አድናት አለው።


ሙሴም ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ ወደ እግዚአብሔርም ለመነ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios