Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 6:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ኢያሪኮም ከእስራኤል ልጆች የተነሣ ፈጽማ ተዘግታ ነበር፥ ወደ እርስዋ የሚገባ ከእርስዋም የሚወጣ ማንም አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በዚህ ጊዜ እስራኤላውያንን ከመፍራት የተነሣ፣ ኢያሪኮ ፈጽማ ተዘግታ ነበር፤ ወደ ውጭ የሚወጣም ሆነ ወደ ውስጥ የሚገባ አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ኢያሪኮም ከእስራኤል ልጆች የተነሣ ፈጽማ ተዘግታ ነበር፤ ወደ እርሷ የሚገባ ከእርሷም የሚወጣ ማንም አልነበረም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እስራኤላውያንን ከመፍራት የተነሣ የኢያሪኮ ቅጽር በሮች ተዘግተው ነበር፤ ወደ ከተማይቱ መግባትም ሆነ መውጣት የሚችል ማንም አልነበረም፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ኢያ​ሪ​ኮም በግ​ንብ ታጥራ ተዘ​ግታ ነበር፤ ወደ እር​ስዋ የሚ​ገባ፥ ከእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ወጣ አል​ነ​በ​ረም።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 6:1
12 Referencias Cruzadas  

ዳዊትም ያን በሰማ ጊዜ ሰዎቹ እጅግ አፍረው ነበሩና ተቀባዮች ላከ። ንጉሡም፦ ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ ተቀመጡ፥ ከዚያም በኋላ ተመለሱ አላቸው።


የአሦርም ንጉሥ በሆሴዕ ላይ ዐመፅ አገኘ፤ መልእክተኞችን ወደ ግብጽ ንጉሥ ወደ ሴጎር ልኮ ነበርና፤ እንደ ልማዱም በየዓመቱ ለአሦር ንጉሥ ግብር አልሰጠምና፤ ስለዚህ የአሦር ንጉሥ ይዞ በወህኒ ቤት አሰረው።


ኤልያስም “ኤልሳዕ ሆይ! እግዚአብሔር ወደ ኢያሪኮ ልኮኛልና እባክህ፥ በዚህ ቆይ፤” አለው። እርሱም “ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ አልለይህም” አለ። ወደ ኢያሪኮም መጡ።


ከኢያኖክም ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ወረደ፥ ወደ ኢያሪኮም ደረሰ፥ ወደ ዮርዳኖስም ወጣ።


የብንያምም ልጆች ነገድ ከተሞች በየወገኖቻቸው እነዚህ ነበሩ፥ ኢያሪኮ፥ ቤትሖግላ፥ ዓመቀጺጽ፥


የነዌም ልጅ ኢያሱ፦ ሄዳችሁ ምድሪቱንና ኢያሪኮን እዩ ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር ላከ። ሄዱም፥ ረዓብም ወደሚሉአት ጋለሞታ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ።


ኢያሱንም፦ በእውነት እግዚአብሔር አገሩን ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶአል፥ በአገሩም ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ በፊታችን ይቀልጣሉ አሉት።


ሰዎቹም ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ በሚወስደው መንገድ አሳደዱአቸው፥ አሳዳጆችም ከወጡ በኋላ በሩ ተቈለፈ።


የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን፦ አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው። ኢያሱም እንዲሁ አደረገ።


እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፦ ተመልከት፥ ኢያሪኮንና ንጉሥዋን ጽኑዓን ኃያላንዋንም በእጅህ ሰጥቼአለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos