Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢያሱ 24:18 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ፥ በምድሪቱ የተቀመጡትን አሞራውያን ከፊታችን አሳደደ፥ ስለዚህ እርሱ አምላካችን ነውና እግዚአብሔርን እናመልካለን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እንዲሁም እግዚአብሔር በምድሪቱ የሚኖሩትን አሞራውያንን ጨምሮ ሕዝቦችን ሁሉ ከፊታችን አሳደደ፤ ስለዚህ እኛም እግዚአብሔርን እናመልካለን፤ አምላካችን ነውና።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ጌታ አሕዛብን ሁሉ፥ በምድሪቱ የተቀመጡትን አሞራውያን ከፊታችን አሳደደ፤ ስለዚህ እርሱ አምላካችን ነውና ጌታን እናገለግላለን።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እግዚአብሔር ሕዝቦችን እንዲሁም በምድሪቱ የሚኖሩትን አሞራውያንን ሁሉ ከፊታችን አባሮልናል፤ ስለዚህም እርሱ አምላካችን ስለ ሆነ እግዚአብሔርን እናመልካለን።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሕ​ዛ​ብን ሁሉ፥ በም​ድ​ሪ​ቱም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ከፊ​ታ​ችን አሳ​ደደ፤ ስለ​ዚህ እርሱ አም​ላ​ካ​ችን ነውና እኛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ካ​ለን።”

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 24:18
13 Referencias Cruzadas  

ይህንንም ያደረግሁት ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ ግብፃውያንን እንደቀጣሁና ምን ዓይነት ተአምራትን እንዳደረግሁ መንገር ትችሉ ዘንድ ነው፤ በዚህም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


ጉልበቴ ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፤ መድኃኒቴም ሆነልኝ፤ ይህ አምላኬ ነው አመሰግነውማለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው ከፍ ከፍም አደርገዋለሁ።


ድንበርህንም ከኤርትራ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፥ ከምድረ በዳም እስከ ወንዙ ድረስ አደርጋለሁ፤ በምድር የሚኖሩትን በእጅህ እጥላለሁና፤ ከፊትህም ታባርራቸዋለሁ።


ከጽዮን ሕግ፥ ከኢየሩሳሌምም የእግዚአብሔር ቃል ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፦ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፥ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በፍለጋውም እንሄዳለን ይላሉ።


የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ዘመን ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ አሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከእናንተ ጋር እንሂድ ይላሉ።


አባቶቻችንም ደግሞ በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር በፊታቸው ያወጣቸውን የአሕዛብን አገር በያዙት ጊዜ ከኢያሱ ጋር አገቡአት፥ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ ኖረች።


ዓይኖችህ ያዩትን እነዚህን ታላላቆች የሚያስፈሩትንም ነገሮች ያደረገልህ እርሱ ክብርህ ነው፥ እርሱም አምላክህ ነው።


መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥ 2 የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤ 2 ጠላትህን ከፊትህ አውጥቶ፦ 2 አጥፋው ይላል።


እግዚአብሔር ታላላቆችንና ኃይለኞችን አሕዛብ ከፊታችሁ አስወጥቶአል፥ እስከ ዛሬም ድረስ ማንም ሊቋቋማችሁ አልቻለም።


እኛንና አባቶቻችንን ከባርነት ቤት ከግብፅ ምድር ያወጣን፥ በዓይናችንም ፊት እነዚያን ታላላቅ ተአምራት ያደረገ፥ በሄድንባትም መንገድ ሁሉ ባለፍንባቸውም አሕዛብ ሁሉ መካከል የጠበቀን፥ እርሱ አምላካችን እግዚአብሔር ነውና።


ኢያሱም ሕዝቡን፦ እርሱ ቅዱስ አምላክ ነውና፥ እርሱም ቀናተኛ አምላክ ነውና እግዚአብሔርን ማምለክ አትችሉም፥ መተላለፋችሁንና ኃጢአታችሁን ይቅር አይልም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos