Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዩኤል 3:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አሕዛብን ሁሉ ሰብስቤ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፥ በዚያም ስለ ሕዝቤና ስለ ርስቴ ስለ እስራኤል በአሕዛብ መካከል የበተኑአቸውን ምድሬንም የተካፈሉአትን እፋረድባቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አሕዛብን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ወደ ኢዮሣፍጥም ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፤ ስለ ርስቴ፣ ስለ ሕዝቤ፣ ስለ እስራኤል፣ በዚያ ልፈርድባቸው እገባለሁ፤ ምድሬን ከፋፍለዋል፤ ሕዝቤንም በሕዝቦች መካከል በታትነዋልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አሕዛብን ሁሉ ሰብስቤ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፥ በዚያም ስለ ሕዝቤና ስለ ርስቴ ስለ እስራኤል በአሕዛብ መካከል የበተኑአቸውን፥ ምድሬንም የተካፈሉአትን እፈርድባቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 አሕዛብን ሁሉ ሰብስቤ፥ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፤ የእኔ የሆኑትን ሕዝቤን እስራኤልን በሕዝቦች መካከል ስለ በታተኑና ምድሪቱን ስለ ተካፈሉ በኢዮሣፍጥ ሸለቆ ወደ ፍርድ አቀርባቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አሕ​ዛ​ብን ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም ሸለቆ አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል በተ​በ​ተ​ኑ​በ​ትና ምድ​ሬን በተ​ካ​ፈ​ሉ​በት በዚያ ስለ ወገ​ኖች ስለ ርስቴ ስለ እስ​ራ​ኤል እወ​ቅ​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዩኤል 3:2
30 Referencias Cruzadas  

በአራተኛውም ቀን በበረከት ሸለቆ ውስጥ ተሰበሰቡ፤ በዚያም እግዚአብሔርን ባረኩ፤ ስለዚህም ያ ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ የበረከት ሸለቆ ተባለ።


እግዚአብሔርም በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ በእሳትና በሰይፉ ይፈርዳል፥ በእግዚአብሔርም ተወግተው የሞቱት ይበዛሉ።


ሥራቸውንና አሳባቸውን አውቄአለሁና፥ አሕዛብንና ልሳትን ሁሉ የምሰበስብበት ጊዜ ይደርሳል፥ እነርሱም ይመጣሉ ክብሬንም ያያሉ።


እግዚአብሔር ለሕዝቤ ለእስራኤል ያወረስሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጐረቤቶች ሁሉ እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፥ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ።


እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ክርክር አለውና ድምፅ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል፥ ከሥጋ ለባሽ ሁሉ ጋር ይፋረዳል፥ ኃጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።


ስለ አሞን ልጆች፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለእስራኤል ልጆች የሉትምን? ወይስ ወራሽ የለውምን? ስለ ምን ሚልኮም ጋድን ወረሰ? ሕዝቡስ በከተሞቹ ላይ ስለ ምን ተቀመጠ?


እስራኤል የባዘነ በግ ነው፥ አንበሶች አሳደዱት፥ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሞዓብና ሴይር፦ እነሆ፥ የይሁዳ ቤት እንደ አሕዛብ ሁሉ ነው ብለዋልና


በጎቼ በተራሮች ሁሉና በረዘሙ ኮረብቶች ሁሉ ላይ ተቅበዝብዘዋል፥ በጎቼም በምድር ፊት ሁሉ ላይ ተበትነዋል፥ የሚሻም የሚፈልግም አልነበረም።


እግዚአብሔርም በዚያ ሳለ፥ አንተ፦ እነዚህ ሁለቱ ሕዝቦች እነዚህም ሁለቱ አገሮች ለእኔ ይሆናሉ እኛም እንወርሳቸዋለን ብለሃልና


አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ተራሮች ትንቢት ተናግረህ፦ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ በል።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በሰጡ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንዓቴ እሳት ተናግሬአለሁ፥


በቸነፈርና በደም እፈርድበታለሁ፥ ዶፍም የበረዶም ድንጋይ እሳትና ድኝም በእርሱና በጭፍሮቹ ከእርሱም ጋር ባሉ በብዙ ሕዝብ ላይ አዘንባለሁ።


በዚያም ቀን በእስራኤል ዘንድ በባሕር ምሥራቅ የሚያልፉበትን ሸለቆ የመቃብርን ስፍራ ለጎግ እሰጣለሁ፥ የሚያልፉትንም ይከለክላል፥ በዚያም ጎግንና ብዛቱን ሁሉ ይቀብራሉ፥ የሸለቆውንም ስም ሐሞንጎግ ብለው ይጠሩታል።


አሕዛብ ይነሡ፥ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆም ይውጡ፥ በዙሪያ ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ እፈርድ ዘንድ በዚያ እቀመጣለሁና።


የእግዚአብሔር ቀን በፍርድ ሸለቆ ቀርቦአልና የብዙ ብዙ ሕዝብ ውካታ በፍርድ ሸለቆ አለ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወንድሙን በሰይፍ አሳድዶታልና፥ ርኅራኄንም ሁሉ ጥሎአልና፥ ቍጣውም ሁልጊዜ ቀድዶአልና፥ መዓቱንም ለዘላለም ጠብቆአልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የኤዶምያስ ኃጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።


ነገር ግን የእግዚአብሔርን አሳብ አያውቁም፥ ምክሩንም አያስተውሉም፥ እንደ ነዶ ወደ አውድማ አከማችቶአቸዋልና።


መዓቴንና የቍጣዬን ትኵሳት ሁሉ አፈስስባቸው ዘንድ ፍርዴ አሕዛብን ለመሰብሰብ፥ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነውና፥ ምድርም ሁሉ በቅንዓቴ እሳት ትበላለችና ስለዚህ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።


አሕዛብም ተቈጡ፥ ቍጣህም መጣ፥ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፥ ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ።


ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደ ሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።


በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ እስከተቱአቸው።


የቅዱሳንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፥ የሚገባቸው ነውና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።


በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ፥ ጎግንና ማጎግን፥ እንዲያስታቸው ለሰልፍም እንዲያስከትታቸው ይወጣል፤ ቍጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ የሚያህል ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios