La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መጽሐፈ ሲራክ 41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
መጽሐፈ ሲራክ 41

ስለ ሞት

1 ሞት ሆይ፥ ሰው በደ​ኅና ሲኖር፥ በሁሉ ተዘ​ጋ​ጅቶ ሳለ፥ ኀይ​ልም ሳለው፥ ለመ​ብ​ላ​ትም ሆዱ ተከ​ፍቶ ሳለ፥ በሰው ላይ በም​ት​መጣ ጊዜ ስም አጠ​ራ​ርህ እን​ዴት መራራ ነው!

2 ሞት ሆይ፥ ኀይል በሌ​ለው፥ ፈጽ​ሞም ባረጀ፥ ሊያ​ደ​ር​ገ​ውም የሚ​ችል ምንም በሌ​ለው፥ የሚ​ያ​ው​ቀ​ውም በሌ​ለው፥ በድሃ ሰው ላይ በም​ት​መጣ ጊዜ ፍር​ድህ እን​ዴት መል​ካም ነው!

3 የሞ​ትን ፍርድ አት​ፍራ፤ ከአ​ን​ተም በፊት የነ​በ​ሩ​ት​ንና ከአ​ን​ተም በኋላ የሚ​ነ​ሡ​ትን አስ​ባ​ቸው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ በሰው ሁሉ ላይ ነው፤

4 እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈቃድ ለምን ትነ​ቅ​ፋ​ለህ? ዐሥር ዓመት፥ መቶ ዓመት፥ ሺህ ዓመ​ትም በሕ​ይ​ወት ብት​ኖር፥ ከሞት ጋራ ክር​ክር የለ​ህም።

5 የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ሰዎች ልጆች ጐስ​ቋ​ሎች ልጆች ይሆ​ናሉ፤ የክ​ፉ​ዎች ሰዎ​ችም ቤታ​ቸው ይፈ​ር​ሳል።

6 የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ልጆች ርስ​ታ​ቸ​ውን ያጣሉ፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ከዘ​ራ​ቸው ጋር አደገ።

7 ስለ እርሱ ይዋ​ረ​ዳ​ሉና፥ የኀ​ጢ​አ​ተኛ አባት ልጆች ይጐ​ሰ​ቍ​ላሉ።

8 የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ላፈ​ረ​ሳ​ችሁ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ሰዎች ወዮ​ላ​ችሁ!

9 ብት​ወ​ል​ዱም ለር​ግ​ማን ትወ​ል​ዳ​ላ​ቸሁ፤ ብት​ሞ​ቱም ዕድል ፋን​ታ​ችሁ ርግ​ማን ነው።

10 ሁሉ ከም​ድር ተፈ​ጠረ፤ መመ​ለ​ሻ​ውም ወደ ምድር ነው፤ ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ችም እን​ዲሁ ከር​ግ​ማን ወደ ጥፋት ይሄ​ዳሉ።

11 የሰው ኀዘኑ ስለ ሰው​ነቱ ነው፤ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም ስማ​ቸው ይደ​መ​ሰ​ሳል።

12 መል​ካም ስምን ታስ​ጠራ ዘንድ አስብ፤ ከሺህ ታላ​ላቅ የወ​ርቅ መዛ​ግ​ብ​ትም እርሱ ብቻ ይቀ​ር​ሃል።

13 በዘ​መ​ንህ ቍጥር በደ​ስታ መኖር መል​ካም ነው፤ እርሱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጸንቶ ይኖ​ር​ል​ሃ​ልና መል​ካም ስም ይሻ​ላል።

14 ጥበብ ግን ልጆ​ች​ዋን በሰ​ላም ትጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋ​ለች፤ የተ​ሰ​ወረ ጥበ​ብና የማ​ይ​ታይ ድልብ፥ የሁ​ለቱ ጥቅ​ማ​ቸው ምን​ድን ነው?

15 ጥበ​ቡን ከሚ​ሰ​ውር ሰው፤ ስን​ፍ​ና​ውን የሚ​ሰ​ውር ሰው ይሻ​ላል።

16 እን​ግ​ዲህ ቃሌ​ንና ጥበ​ቤን እፈሩ፤ የሚ​ያ​ፍር ሁሉ በበጎ ይጠ​በ​ቃል፤ በሁሉ ይማ​ከር ዘንድ ሁሉ የታ​መነ አይ​ደ​ለም።

17 ልጅ እን​ወ​ል​ዳ​ለን ብለው በዝ​ሙት መኖር፤ ለአ​ባ​ትና ለእ​ናት ኀፍ​ረት ነው ለአ​ለ​ቃና ለታ​ላ​ላ​ቆ​ችም መዋ​ሸት ኀፍ​ረት ነው።

18 ለሹ​ምና ለዳኛ ቃል መለ​ወጥ ኀፍ​ረት ነው። ለማ​ኅ​በ​ርና ለሕ​ዝ​ብም መሳት ኀፍ​ረት ነው፤ ከጓ​ደ​ኛ​ህና ከወ​ዳ​ጅህ ጋር መከ​ዳ​ዳት ኀፍ​ረት ነው።

19 ለእ​ን​ግዳ በእ​ን​ግ​ድ​ነት ካደ​ረ​በት ቤት ሰርቆ መሄድ ኀፍ​ረት ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እው​ነ​ትና ቃል ኪዳን ማፍ​ረስ ኀፍ​ረት ነው፤ የሌላ ሰው እህል ለመ​ብ​ላት በመ​ስ​ገ​ብ​ገብ መቅ​ረብ ኀፍ​ረት ነው፤ አደራ ከአ​ስ​ጠ​በ​ቁህ ገን​ዝ​ብና ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ገን​ዘብ መስ​ረቅ ኀፍ​ረት ነው።

20 የሚ​ጠ​ራ​ህን ሰው ቸል ማለት ኀፍ​ረት ነው፤ ወደ ሌላ ሰው ሚስ​ትም መመ​ል​ከት ኀፍ​ረት ነው።

21 በመ​ከ​ራው ጊዜ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን ቸል ማለት ኀፍ​ረት ነው፤ በሌላ ሰው ገን​ዘ​ብም መሳ​ሳት ኀፍ​ረት ነው። የጎ​ል​ማሳ ሚስት ማነ​ጋ​ገ​ርም ኀፍ​ረት ነው።

22 ገረ​ዱ​ንም አታ​ባ​ብ​ላት፤ ወደ መኝ​ታ​ዋም አት​ቅ​ረብ፤ ወዳ​ጅ​ህን መሳ​ደብ ኀፍ​ረት ነው፤ ከሰ​ጠ​ኸ​ውም በኋላ አት​ሳ​ደብ፤ የሰ​ማ​ኸ​ውን ነገር ማው​ጣት፥ መና​ገ​ርም ኀፍ​ረት ነው። ምሥ​ጢ​ር​ንም መግ​ለጥ ኀፍ​ረት ነው፤

23 ይህን ብት​ጠ​ብቅ በእ​ው​ነት ኀፊረ ገጽ ያለህ ትሆ​ና​ለህ፤ በሰ​ውም ሁሉ ዘንድ መወ​ደ​ድን ታገ​ኛ​ለህ።