La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መጽሐፈ ሲራክ 40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
መጽሐፈ ሲራክ 40

የሰ​ብ​አዊ ሕይ​ወት ችግር

1 የሰው የተ​ፈ​ጥ​ሮው መከራ ታላቅ ነው፤ ከእ​ና​ታ​ቸው ማኅ​ፀን ከሚ​ወ​ጡ​በት ጀምሮ በሁሉ እናት ሆድ እስ​ኪ​ቀ​በሩ ድረስ በአ​ዳም ልጆች ላይ ከባድ ሸክም አለ።

2 ዕለተ ሞትን ማሰብ በአ​ዳም ልጆች ሁሉ ላይ የም​ታ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጥና ልብ​ንም የም​ታ​ስ​ፈራ ናት።

3 በመ​ን​ግ​ሥት ዙፋን ከሚ​ቀ​መጥ ንጉሥ ጀምሮ በዐ​መ​ድና በት​ቢያ ላይ እስ​ከ​ሚ​ተኛ ድሃ ድረስ፥

4 ቀይ ግምጃ ከሚ​ለ​ብ​ስና ዘውድ ከሚ​ቀ​ዳጅ ጀምሮ የተ​ናቀ ልብ​ስን እስ​ከ​ሚ​ለ​ብስ ድረስ፥

5 ቍጣና ቅን​ዓት፥ ንዝ​ን​ዝና ሁከት፥ ሞትን መፍ​ራ​ትና ክር​ክር፥ ሐሜ​ትም አለ፤ በመ​ኝ​ታው በተኛ ጊዜ የሌ​ሊት እን​ቅ​ልፍ አሳ​ቡን ይለ​ው​ጠ​ዋል።

6 ዕረ​ፍቱ ጥቂት ወይም እንደ ኢም​ንት ነው፤ ይህ ሁሉ በመ​ኝ​ታው ይታ​ወ​ቃል፤ አንድ ጊዜ እንደ ሸንጎ ተከ​ማ​ችቶ ያገ​ኘ​ዋል፤ ከሰ​ልፍ እን​ደ​ሚ​ሸሽ ሰውም የል​ቡ​ና​ውን ምክር ያወ​ላ​ው​ላ​ታል።

7 የሸ​ሸው ሰው ግን ዕለ​ቱን ያመ​ል​ጣል፤ ፍር​ሀ​ቱ​ንም እርሱ ራሱ ያደ​ን​ቃ​ታል፤

8 ይህ ሁሉ በሰው ላይ እስከ እን​ስሳ ድረስ አለ፤ ይህም በኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ሰዎች ላይ ሰባት እጥፍ ይብ​ሳል።

9 ሞትና መታ​በይ፥ ቸነ​ፈ​ርና ጦር​ነት፥ ቀጠ​ናና የልብ ቍስል፥ መቅ​ሠ​ፍ​ትም።

10 ይህ ሁሉ በኀ​ጢ​አ​ተኛ ስዎች ላይ ተፈ​ጠረ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ምክ​ን​ያት የጥ​ፋት ውኃ መጣ።

11 ሁሉ ከም​ድር ተፈ​ጠረ፤ ሁሉም ወደ ምድር ይመ​ለ​ሳል፤ የወ​ንዙ ውኃ ሁሉ ወደ ውቅ​ያ​ኖስ ይመ​ለ​ሳል።

የክ​ፋት ውጤት

12 መማ​ለ​ጃና ዐመፃ ሁሉ ይደ​መ​ሰ​ሳሉ፤ ሃይ​ማ​ኖት ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ ትጸ​ና​ለች።

13 የዐ​መፃ ገን​ዘብ እንደ ፈሳሽ ውኃ ይደ​ር​ቃል፤ በዘ​ነ​በም ጊዜ እንደ ታላቅ መብ​ረቅ ጩሆ ይጠ​ፋል።

14 እርሱ እጁን ከዘ​ረጋ ደስ ያሰ​ኛል፤ የሚ​ክ​ዱት ሰዎች ግን ፈጽ​መው ይጠ​ፋሉ።

15 የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ልጆች ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቻ​ቸው አይ​በ​ዙም፤ የር​ኩ​ሳን ሰዎች ሥራ​ቸው በሚ​ያ​ድጥ ዓለት ላይ እንደ ወደቀ ዘር ነው።

16 በው​ኃና በወ​ንዝ ዳር የበ​ቀለ አረ​ምም ከሣሩ ሁሉ ቀድሞ ይነ​ቀ​ላል።

17 ጸጋ ግን በበ​ረ​ከት እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነት ናት፥ ምጽ​ዋ​ትም ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ ጸንቶ ይኖ​ራል።

18 የሚ​ዘ​ጋ​ጅና የሚ​ሠራ ሰው ሕይ​ወቱ ጣፋጭ ነው፤ ከእ​ነ​ዚ​ህም ከሁ​ለቱ ይልቅ የተ​ቀ​በረ ወር​ቅን ማግ​ኘት ደስ ያሰ​ኛል።

19 ልጆ​ችና የሀ​ገር ሕንጻ ስምን ያስ​ጠ​ራሉ፤ ከእ​ነ​ዚህ ከሁ​ለቱ ይልቅ ምንም ነውር የሌ​ለ​ባት ሴት ደስ ታሰ​ኛ​ለች።

20 ወይ​ንና ማሕ​ሌት ልብን ደስ ያሰ​ኛሉ፥ ከሁ​ለ​ቱም ይልቅ ጥበ​ብን መው​ደድ ደስ ያሰ​ኛል።

21 በገ​ናና መሰ​ንቆ ሰው​ነ​ትን ደስ ያሰ​ኙ​ኣ​ታል፤ ከሁ​ለ​ቱም ይልቅ ልዝብ አን​ደ​በት ደስ ያሰ​ኛል።

22 ደም ግባ​ትና ውበት ዐይ​ንን ደስ ያሰ​ኙ​ኣ​ታል። ከሁ​ለ​ቱም ይልቅ ቡቃያ ደስ ያሰ​ኛል።

23 ወዳ​ጅና ጓደኛ በዘ​መ​ና​ቸው ይጠ​ቅ​ማሉ፤ ከሁ​ለ​ቱም ይልቅ ደግ ሴት ባሏን ትጠ​ቅ​ማ​ለች።

24 ወን​ድ​ሞ​ችና ረዳት በመ​ከራ ቀን ይጠ​ቅ​ማሉ፤ ከሁ​ለ​ቱም ይልቅ ለማ​ዳን ምጽ​ዋት ትበ​ል​ጣ​ለች።

25 ወር​ቅና ብር ሀገ​ርን ያጸ​ናሉ፤ ከሁ​ለ​ቱም ይልቅ በጎ ምክር ደስ ታሰ​ኛ​ለች።

26 ባለ​ጸ​ግ​ነ​ትና ገን​ዘብ ልቡ​ናን ደስ ያሰ​ኛሉ፤ ከሁ​ለ​ቱም ይልቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ደስ ያሰ​ኛል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት የም​ታ​ሳ​ጣው የለም፤ አጋ​ዥም አት​ሻም።

27 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት በበ​ረ​ከ​ትዋ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነት ናት፤ ክብ​ርና ደስ​ታም ሁሉ በእ​ር​ስዋ አለ።

28 ልጄ ሆይ! በጉ​ል​በ​ትህ ሳለህ ልመ​ናን አት​ው​ደ​ዳት፤ ከመ​ለ​መን መሞት ይሻ​ላል።

29 የሌላ ማዕድ ደጅ የሚ​ጠ​ናና ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው፤ ኑሮው እንደ ሞተ ሰው ነው፤ የሰው እህል የሚ​ወድ ሰው ከሐ​ሜት አይ​ድ​ንም፤ የተ​መ​ከረ ብልህ ሰው ግን ከሁሉ ይጠ​በ​ቃል።

30 ለማ​ያ​ፍር ሰው አፍ ልመና ጣፋጭ ነው፤ በሆዱ ግን እሳት ትነ​ድ​ዳ​ለች።