La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


ትን​ቢተ ዳን​ኤል 6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ትን​ቢተ ዳን​ኤል 6

በዳ​ን​ኤል ላይ የተ​ደ​ረገ ሤራ

1 ዳር​ዮ​ስም በመ​ን​ግ​ሥቱ ሁሉ ዘንድ እን​ዲ​ሆኑ መቶ ሃያ መሳ​ፍ​ን​ትን በመ​ን​ግ​ሥቱ ላይ ይሾም ዘንድ ወደደ።

2 መሳ​ፍ​ን​ቱም ግብ​ሩን ያመ​ጡ​ላ​ቸው ዘንድ፥ ንጉ​ሡም በማ​ን​ኛ​ውም እን​ዳ​ይ​ቸ​ገር ሦስት አለ​ቆች በላ​ያ​ቸው አደ​ረገ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ደ​ኛው ዳን​ኤል ነበረ።

3 ዳን​ኤ​ልም መል​ካም መን​ፈስ ስለ አለው ከአ​ለ​ቆ​ችና ከመ​ሳ​ፍ​ንት በለጠ፤ ንጉ​ሡም በመ​ን​ግ​ሥቱ ሁሉ ላይ ሾመው።

4 ያን ጊዜም አለ​ቆ​ችና መሳ​ፍ​ንቱ ስለ መን​ግ​ሥቱ በዳ​ን​ኤል ላይ ምክ​ን​ያት ይፈ​ልጉ ነበር፤ ነገር ግን የታ​መነ ነበ​ረና፥ ምንም በደል አል​ተ​ገ​ኘ​በ​ት​ምና በእ​ርሱ ላይ ሰበ​ብና በደል ያገ​ኙ​በት ዘንድ አል​ቻ​ሉም።

5 እነ​ዚ​ያም ሰዎች፥ “ከአ​ም​ላኩ ሕግ በቀር በዚህ በዳ​ን​ኤል ላይ ሌላ ምክ​ን​ያት አና​ገ​ኝ​በ​ትም” አሉ።

6 ያን ጊዜም ሹሞ​ቹና መኳ​ን​ንቱ ወደ ንጉሡ ተሰ​ብ​ስ​በው እን​ዲህ አሉት፥ “ንጉሥ ዳር​ዮስ ሆይ! ለዘ​ለ​ዓ​ለም ኑር።

7 የመ​ን​ግ​ሥቱ አለ​ቆች ሁሉ ሹሞ​ችና መሳ​ፍ​ንት፥ አማ​ካ​ሪ​ዎ​ችና አዛ​ዦች፦ ንጉሥ ሆይ! ከአ​ንተ በቀር ማንም እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ልመና ከአ​ም​ላክ ወይም ከሰው ቢለ​ምን፥ በአ​ን​በ​ሶች ጕድ​ጓድ ውስጥ ይጣል የሚል የን​ጉሥ ሕግና ብርቱ ትእ​ዛዝ ይወጣ ዘንድ ተማ​ከሩ።

8 አሁ​ንም ንጉሥ ሆይ! እን​ደ​ማ​ይ​ለ​ወ​ጠው እንደ ሜዶ​ንና እንደ ፋርስ ሕግ እን​ዳ​ይ​ለ​ወጥ ትእ​ዛ​ዙን አጽና፤ ጽሕ​ፈ​ቱ​ንም ጻፍ።”

9 ያን ጊዜም ንጉሡ ዳር​ዮስ ይህን ሥር​ዐት ይጽፉ ዘንድ አዘዘ።

ዳን​ኤል በአ​ን​በሳ ጕድ​ጓድ እንደ ተጣለ

10 ዳን​ኤ​ልም ይህ ሥር​ዐት እንደ ታዘዘ በዐ​ወቀ ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ፤ የእ​ል​ፍ​ኙም መስ​ኮ​ቶች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አን​ጻር ተከ​ፍ​ተው ነበር፤ ቀድ​ሞም ያደ​ርግ እንደ ነበረ ከቀኑ በሦ​ስት ሰዓት በጕ​ል​በቱ ተን​በ​ር​ክኮ በአ​ም​ላኩ ፊት ጸለየ አመ​ሰ​ገ​ነም።

11 እነ​ዚ​ያም ሰዎች በማ​ን​ኛ​ውም ነገር ዘወ​ትር ይመ​ለ​ከ​ቱት ነበ​ርና ዳን​ኤል በአ​ም​ላኩ ፊት ሲጸ​ል​ይና ሲለ​ምን አገ​ኙት።

12 ወደ ንጉ​ሡም ቀር​በው ስለ ንጉሡ ትእ​ዛዝ፥ “ንጉሥ ሆይ! ከአ​ንተ በቀር እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ከአ​ም​ላክ ወይም ከሰው የሚ​ለ​ምን ሰው ሁሉ በአ​ን​በ​ሶች ጕድ​ጓድ ውስጥ እን​ዲ​ጣል ትእ​ዛዝ አል​ጻ​ፍ​ህ​ምን?” አሉት። ንጉ​ሡም መልሶ፥ “ነገሩ እን​ደ​ማ​ይ​ለ​ወ​ጠው እንደ ሜዶ​ንና እንደ ፋርስ ሕግ እው​ነት ነው” አላ​ቸው።

13 የዚ​ያን ጊዜም በን​ጉሡ ፊት መል​ሰው፥ “ንጉሥ ሆይ! ከይ​ሁዳ የም​ርኮ ልጆች የሆ​ነው ዳን​ኤል ከቀኑ በሦ​ስት ሰዓት ልመ​ና​ውን ይለ​ም​ናል እንጂ አን​ተ​ንና የጻ​ፍ​ኸ​ውን ትእ​ዛዝ አይ​ቀ​በ​ልም” አሉት።

14 ንጉ​ሡም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ በጣም አዘነ፤ ያድ​ነ​ውም ዘንድ ልቡን ወደ ዳን​ኤል አደ​ረገ፤ ሊያ​ድ​ነ​ውም ፀሐይ እስ​ኪ​ገባ ድረስ ደከመ።

15 ያን ጊዜም እነ​ዚያ ሰዎች ወደ ንጉሡ ተሰ​ብ​ስ​በው ንጉ​ሡን፥ “ንጉሥ ሆይ! ንጉሡ ያጸ​ናው ትእ​ዛዝ ወይም ሥር​ዐት ይለ​ወጥ ዘንድ እን​ዳ​ይ​ገባ የሜ​ዶ​ንና የፋ​ርስ ሕግ እንደ ሆነ ዕወቅ” አሉት።

16 ያን ጊዜም ዳን​ኤ​ልን አም​ጥ​ተው በአ​ን​በ​ሶች ጕድ​ጓድ ይጥ​ሉት ዘንድ ንጉሡ አዘዘ፤ ንጉ​ሡም ዳን​ኤ​ልን፥ “ሁል​ጊዜ የም​ታ​መ​ል​ከው አም​ላ​ክህ እርሱ ያድ​ንህ” አለው።

17 ድን​ጋ​ይም አም​ጥ​ተው በጕ​ድ​ጓዱ አፍ ላይ ገጠ​ሙ​በት፤ ንጉ​ሡም በዳ​ን​ኤል ላይ የሚ​ተ​ነ​ኳ​ኰል ሰው እን​ዳ​ይ​ኖር በቀ​ለ​በ​ቱና በመ​ኳ​ን​ንቱ ቀለ​በት አተ​መው።

18 ንጉ​ሡም ወደ ቤቱ ሄደ፤ ሳይ​በ​ላም ተኛ፤ የሚ​በ​ላ​ውም አላ​መ​ጡ​ለ​ትም፤ እን​ቅ​ል​ፉም ከእ​ርሱ ራቀ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የአ​ን​በ​ሶ​ቹን አፍ ዘጋ፤ ዳን​ኤ​ል​ንም አል​ቧ​ጨ​ሩ​ትም።

ዳን​ኤል ከአ​ን​በ​ሶች አፍ እንደ ዳነ

19 በነ​ጋ​ውም ንጉሡ ማልዶ ተነሣ፤ ፈጥ​ኖም ወደ አን​በ​ሶች ጕድ​ጓድ ሄደ።

20 ወደ ጕድ​ጓ​ዱም በቀ​ረበ ጊዜ በታ​ላቅ ቃል ጮኸ፤ ንጉ​ሡም ዳን​ኤ​ልን፥ “የሕ​ያው አም​ላክ ባሪያ ዳን​ኤል ሆይ! ሁል​ጊዜ የም​ታ​መ​ል​ከው አም​ላ​ክህ ከአ​ን​በ​ሶች አፍ ያድ​ንህ ዘንድ ችሎ​አ​ልን?” አለው።

21 ዳን​ኤ​ልም ንጉ​ሡን፥ “ንጉሥ ሆይ! ለዘ​ለ​ዓ​ለም ኑር።

22 በፊቱ ቅን​ነት ተገ​ኝ​ቶ​ብ​ኛ​ልና፥ በአ​ን​ተም ፊት ደግሞ፤ ንጉሥ ሆይ! አል​በ​ደ​ል​ሁ​ምና አም​ላኬ መል​አ​ኩን ልኮ የአ​ን​በ​ሶ​ችን አፍ ዘጋ፤ እነ​ር​ሱም አል​ቧ​ጨ​ሩ​ኝም” አለው።

23 ያን ጊዜም ንጉሡ እጅግ ደስ አለው፤ ዳን​ኤ​ል​ንም ከጕ​ድ​ጓዱ ያወ​ጡት ዘንድ አዘዘ፤ ዳን​ኤ​ልም ከጕ​ድ​ጓዱ ወጣ፤ በአ​ም​ላ​ኩም ታምኖ ነበ​ርና አን​ዳች ጕዳት አል​ተ​ገ​ኘ​በ​ትም።

24 ንጉ​ሡም ዳን​ኤ​ልን የከ​ሰሱ እነ​ዚ​ያን ሰዎች ያመ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ አዘዘ፤ እነ​ር​ሱ​ንና ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በአ​ን​በ​ሶች ጕድ​ጓድ ጣሉ​አ​ቸው፤ ወደ ጕድ​ጓ​ዱም መጨ​ረሻ ሳይ​ደ​ርሱ አን​በ​ሶች ያዙ​አ​ቸው፤ አጥ​ን​ታ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ሰባ​በሩ።

25 ያን ጊዜም ንጉሥ ዳር​ዮስ በም​ድር ሁሉ ላይ ወደ​ሚ​ኖሩ ወገ​ኖ​ችና አሕ​ዛብ፥ በልዩ ልዩም ቋንቋ ወደ​ሚ​ና​ገሩ ሁሉ ጻፈ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ሰላም ይብ​ዛ​ላ​ችሁ።

26 በመ​ን​ግ​ሥቴ ግዛት ሁሉ ያሉ ሰዎች በዳ​ን​ኤል አም​ላክ ፊት እን​ዲ​ፈ​ሩና እን​ዲ​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ አዝ​ዣ​ለሁ፤ እርሱ ሕያው አም​ላክ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ኖር ነውና፤ መን​ግ​ሥ​ቱም የማ​ይ​ጠፋ ነው፥ ግዛ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።

27 ያድ​ናል፤ ይታ​ደ​ግ​ማል፤ በሰ​ማ​ይና በም​ድ​ርም ተአ​ም​ራ​ት​ንና ድን​ቅን ይሠ​ራል፤ ዳን​ኤ​ል​ንም ከአ​ን​በ​ሶች አፍ አድ​ኖ​ታል።”

28 ይህም ዳን​ኤል በዳ​ር​ዮስ መን​ግ​ሥ​ትና በፋ​ር​ሳ​ዊው በቂ​ሮስ መን​ግ​ሥት ከፍ ከፍ አለ።