መዝሙር 123 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መዝሙር 123ምሕረት ለማግኘት የቀረበ ጸሎት1 እግዚአብሔር ሆይ! ዙፋንህ በሰማይ ወደ ሆነው ወደ አንተ እመለከታለሁ። 2 እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! አገልጋዮችና ገረዶች የአሳዳሪዎቻቸውን እጅ እንደሚጠባበቁ ሁሉ እኛም እስክትምረን ድረስ የአንተን ምሕረት ለማግኘት እንጠባበቃለን። 3 እግዚአብሔር ሆይ! ብዙ ስድብ ስለ ደረሰብን ማረን! እባክህ ማረን! 4 በትዕቢተኞች ብዙ መዋረድ፥ በትምክሕተኞችም ብዙ መናቅ ደርሶብናል። |