La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


2 ቆሮንቶስ INTRO1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
2 ቆሮንቶስ INTRO1

1

መግቢያ
ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች የጻፈላቸው ሁለተኛው መልእክት የተጻፈው በቆሮንቶስ ከነበረችው ቤተ ክርስቲያን ጋር የነበረው ግንኙነት እጅግ አስቸጋሪ በሆነበት ጊዜ ነው። አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባሎች ከበድ ያሉ ነቀፋዎችን የሰነዘሩበት ቢሆንም ጳውሎስ ዕርቅ ለመፍጠር ታላቅ ፍላጎት እንዳለው ያሳያል፤ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ታላቅ ደስታ ሊሰማው እንደሚችል ይገልጣል።
በመልእክቱ መጀመሪያ ክፍል ላይ ጳውሎስ በቆሮንቶስ ከነበረችው ቤተ ክርስቲያን ጋር ስላለው ግንኙነት በመግለጥ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ለተነሣው ነቀፋና ተቃውሞ ለምን ከረር ያለ መልስ እንደ ሰጣቸው ያስረዳል። ከዚህም በማያያዝ ይህ የእርሱ ተግሣጽ ወደ ንስሓና ወደ ዕርቅ የመራቸው በመሆኑ የተሰማውን ደስታ ይገልጥላቸዋል። ቀጥሎም በይሁዳ ያሉትን ክርስቲያኖች ለመርዳት በለጋሥነት እንዲሰጡ ያሳስባቸዋል። በመጨረሻዎቹ ምዕራፎች ጳውሎስ በሐዋርያነቱ ላይ ስለ ቀረበበት ክስ መከላከያ ይሰጣል። በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን እውነተኞች ሐዋርያት በማድረግ ጳውሎስ ሐሰተኛ ሐዋርያ ነው እያሉ ይከሱት ነበር።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መቅድም 1፥1-11
ጳውሎስና የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን 1፥12—7፥16
በይሁዳ ለሚገኙ ክርስቲያኖች ርዳታ 8፥1—9፥15
ጳውሎስ ለሐዋርያዊ ሥልጣኑ ያቀረበው መከላከል 10፥1—13፥10
ማጠቃለያ 13፥11-14

Mostrar Biblia Interlineal

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia