La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መዝሙር 142 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
መዝሙር 142

የእግዚአብሔርን ርዳታ ለማግኘት የሚቀርብ ጸሎት

1 ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ ምሕረት እንዲያደርግልኝ እለምነዋለሁ።

2 አቤቱታዬን ሁሉ በፊቱ አቀርባለሁ፤ ችግሬንም ሁሉ እነግረዋለሁ።

3 ተስፋ ለመቊረጥ ጥቂት በቀረኝ ጊዜ ምን ማድረግ እንደሚገባኝ ያውቃል፤ ጠላቶቼ በምሄድበት መንገድ ላይ ወጥመድ ዘረጉብኝ።

4 በዙሪያዬ ስመለከት መሸሸጊያ የሚሆነኝ አጣሁ፤ አንድም እንኳ የሚረዳኝ ሰው አልነበረም፤ የሚጠብቀኝና የሚጠነቀቅልኝም አልነበረም።

5 እግዚአብሔር ሆይ! እንድትረዳኝ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ! ጠባቂዬ አንተ ነህ፤ በሕያዋን ምድር ዕድል ፈንታዬ አንተ ነህ።

6 በጣም ተስፋ የቈረጥሁ ስለ ሆነ እንድትረዳኝ ወደ አንተ ስጮኽ ስማኝ፤ እጅግ በርትተውብኛልና ከጠላቶቼ አድነኝ።

7 አመሰግንህ ዘንድ ከእስራቴ አውጣኝ፤ ለእኔ ያደረግኸውን ያንተን የቸርነት ሥራ በሚያዩበት ጊዜ ሕዝብህ በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ።

Mostrar Biblia Interlineal

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia