እግዚአብሔር እርሷን ካልሰጠኝ በቀር እንደማላገኛት በዐወቅሁ ጊዜ ይህ ምክር ከጥበብ ሆነ፤ የማን ስጦታም እንደ ሆነች ዐውቅ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ፥ ለመንሁትም።
ነገር ግን ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ጥበብን ማግኘት እንደማይቻል በመረዳቴ፥ ጥበብ የማን ስጣታ እንደ ሆነች መረዳቱ ራሱ የማስተዋል ምልክት ነው። ወደ ጌታ ጸለይሁ፥ ተማፀንሁት፥ ከልቤም እንዲህ አልሁ፦