በዚህ ግን በስንፍናና በኀጢአት የኖሩ በደለኞች ሰዎችን ቀጣህ፥ በየራሳቸውም ኀጢአት ፈረድህባቸው።
ከንቱና ክፋት የተሞላበት ሕይወት የሚመሩ ሰዎች በገዛ ራሳቸው መጥፎ ተግባር እንዲሠቃዩ ያደረግኸውም ለዚሁ ነው።