እንዲህ ባለ ሥራም ጻድቅ ሰው ርኅሩኅና ሰው ወዳጅ መሆን ይገባው ዘንድ ወገኖችህን አስተማርህ፤ ለልጆችህም በጎ ተስፋን አደረግህ፥ አንተ ለበደለኛ ንስሓን ትሰጣለህና።
እንዲህ በማድረግህ ሕዝብህን አስተማርህ፤ ጻድቅ ሰው ለሌሎች ደግ መሆን እንዳለበት ገለጽህ፤ ለልጆችህ መልካም ተስፋን፥ ለኃጢአታቸውም ንስሐን ሰጠሃቸው።