ዓለሙ ሁሉ በፊትህ እንደ ሚዛን ውልብልቢት ነውና፥ በማለዳም በምድር ላይ እንደ ወረደች እንደ ጠል ጠብታ ነውና።
አንተ ግን ሁሉን ቻይ በመሆንህ፥ ምሕረትህ ለሰዎች ሁሉ ነው፤ ሰዎች ቢበድሉም ይጸጸቱ ዘንድ ታልፋቸዋለህ።