የብርታትና የኀይል ሁሉ አምላክ አንተ እግዚአብሔር እንደ ሆንህ፥ የእስራኤልንም ወገን ከአንተ በቀር ሌላ የሚያጸናቸው እንደ ሌለ ለሕዝቡና ለአሕዛቡ ሁሉ እንዲያውቁት አድርግ።”
ሕዝቦችህ ሁሉና ነገዶች ሁሉ፥ አምላክ አንተ ብቻ እንደሆንህ፥ ከሁሉም በላይ የኃያልና የብርታት አምላክ፥ ከአንተ በቀር እስራኤልን የሚታደግ ሌላ እንደሌለ እንዲያውቁ አድርግ።