መሥዋዕቱ ሁሉ ለበጎ መዓዛ አይበቃምና፥ ስቡም ሁሉ ከቍርባንህ ያንሣልና። እግዚአብሔርን የሚፈራው ሰው ግን ሁልጊዜ ገናና ነው።
ዮዲትም ሕዝቡ የሰጣትን የሆሎፎርኒስን ንብረቶች ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበች። ከመኝታ ቤቱ ያመጣችውን መጋረጃ እንደ ስእለት አድርጋ ለጌታ ሰጠች።