ሁላችሁም የጦር መሣሪያችሁን ያዙ፥ ዘበኞችም ባዩአችሁ ጊዜ የአሦር ሠራዊት አለቆችን ይቀሰቅሱ ዘንድ ወደ ሰፈራቸው ይሄዳሉ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሆሎፎርኒስ ድንኳን ይሮጣሉ፤ አያገኙትም፤ ከዚያም በኋላ እጅግ ፈርተው ከፊታችሁ ይሸሻሉ።
የጦር መሣሪያቸውን ይዘው ወደ ጦር ሰፈራቸው ይሄዳሉ፤ የአሦርን የጦር ሠራዊት አዛዦችን ይቀሰቅሳሉ፤ ወደ ሆሎፎርኒስ ድንኳን ይሮጣሉ፥ ነገር ግን አያገኙትም። በዚያን ጊዜ ፍርሃት ይይዛቸዋል፥ ከፊታችሁም ይሸሻሉ።