እንደ ተመለሰችም አድንቀዋልና ታናሹም፥ ታላቁም ሁሉ ሮጠው ሄዱ፤ በሩንም ከፍተው ተቀበሏት፤ እሳትም አንድደው፥ ፋና አብርተው ከበቧት።
መመለሷ የማይታሰብ ነበርና ከትልቁ እስከ ትንሹ ሁሉም እየሮጡ መጡ። በሩንም ከፍተው ተቀበሏቸው፤ ብርሃን እንዲሆን እሳት አንድደው ዙሪያቸውን ከበቡአቸው።