ዮዲትም ወደ እርሱ ገብታ ተቀመጠች፤ የሆሎፎርኒስም ልቡናው በእርሷ ታወከ፤ ከእርሷም ጋር ይተኛ ዘንድ ሰውነቱ ፈጽማ ጐመጀች፤ ከአያትም ጀምሮ እርሷን እስከሚያባብልበት ጊዜ ይጠብቃት ነበር።
ዮዲትም ገብታ ተቀመጠች፤ የሆሎፎርኒስ ልብ ተደነቀች፤ ከእርሷም ጋር ለመተኛት ነፍሱ ፈጽማ ታወከች፤ እርሷን ካየበት ቀን ጀምሮ እርሷን ለማሳሳት ምቹ ጊዜ ይፈልግ ነበር፤