እንዲህም አለቻቸው፥ “አሁንም ከእናንተ ጋራ የተናገርሁትንነገር ወጥቼ አደርግ ዘንድ የከተማውን በር የሚከፍትልኝ ሰው እዘዙልኝ፤” እንደ ጠየቀችም ይከፍቱላት ዘንድ ጐልማሶችን አዘዙአቸው።
እርሷም ለእግዚአብሔር ሰገደች፤ እንዲህም አለቻቸው፦ “ከእኔ ጋር የተነጋገራችሁበትን ነገር ወጥቼ እንድፈጽም የከተማይቱን በር እንዲከፈትልኝ እዘዙ።” እርሷ እንደ ጠየቀችው እንዲከፍቱላት ጐልማሶቹን አዘዙአቸው።