ይዘውም መረመሩአት፤ እንዲህም አሏት፥ “አንቺ ማን ነሽ? ከየት መጣሽ? ወዴትስ ትሄጃለሽ?” እርስዋም አለቻቸው፥ “እኔ ከዕብራውያን የተወለድሁ ነኝ፤ ሀገራቸውን ለእናንተ አሳልፈው ሊሰጡ በወደዱ ጊዜ ከእነርሱ ኰብልዬ መጣሁ።
ያዟትና እንዲህ ሲሉ ይጠይቋት ጀመር፦ “ከማን ወገን ነሽ? ከየት ትመጫለሽ? ወዴትስ ትሄጃለሽ?” እርሷም እንዲህ ስትል መለሰችላቸው፤ “እኔ የዕብራውያን ልጅ ነኝ፥ ለእናንተ መብል እንዲሆኑ ተላልፈው ሊሰጡ ስለሆነ ከእነርሱ ፊት ጠፍቼ መጣሁ።