La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 9:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤ​ሜ​ሌ​ክና ከእ​ርሱ ጋር ያሉ​ትም ሕዝብ ሁሉ ወደ ሄር​ሞን ተራራ ወጡ፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክም በእጁ መጥ​ረ​ቢያ ወስዶ የዛ​ፉን ቅር​ን​ጫፍ ቈረጠ፤ አን​ሥ​ቶም በጫ​ን​ቃው ላይ ተሸ​ከ​መው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ለነ​በ​ሩት ሕዝብ፥ “እኔ ሳደ​ርግ ያያ​ች​ሁ​ትን፥ እና​ን​ተም ፈጥ​ና​ችሁ እኔ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ አድ​ርጉ” አላ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱና ሰዎቹ ሁሉ ወደ ሰልሞን ተራራ ወጡ፤ አቢሜሌክም መጥረቢያ ወስዶ ጥቂት የዛፍ ቅርንጫፍ ቈረጠ፤ በትከሻውም ላይ አደረገ። የተከተሉትንም ሰዎች፣ “ፍጠኑ፤ እኔ ሳደርግ ያያችሁትን አድርጉ” ሲል አዘዛቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱና ሰዎቹ ሁሉ ወደ ሰልሞን ተራራ ወጡ፤ አቤሜሌክም መጥረቢያ ወስዶ ጥቂት የዛፍ ቅርንጫፍ ቈረጠ፤ በትከሻውምላይ አደረገ። የተከተሉትንም ሰዎች፥ “ፍጠኑ፤ እኔ ሳደርግ ያያችሁትን አድርጉ” ሲል አዘዛቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም ከተከታዮቹ ጋር ወደ ጻልሞን ተራራ ወጣ፤ ከዚያም መጥረቢያ ወስዶ ከዛፍ ላይ እንጨት በመቊረጥ በትከሻው ተሸከመ፤ ተከታዮቹም በፍጥነት እርሱ እንዳደረገው ያደርጉ ዘንድ ነገራቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አቤሜሌክና ከእርሱ ጋር ያሉትም ሕዝብ ሁሉ ወደ ሰልሞን ተራራ ወጡ፥ አቤሜሌክም በእጁ መጥረቢያ ወስዶ የዛፉን ቅርንጫፍ ቈረጠ፥ አንሥቶም በጫንቃው ላይ አደረገው፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት ሕዝብ፦ እኔ ሳደርግ ያያችሁትን፥ እናንተም ፈጥናችሁ እኔ እንዳደረግሁ አድርጉ አላቸው።

Ver Capítulo



መሳፍንት 9:48
7 Referencias Cruzadas  

እን​ዳ​ይ​ው​ጠኝ ከረ​ግ​ረግ አው​ጣኝ፤ ከጠ​ላ​ቶ​ችና ከጥ​ልቅ ውኃ አስ​ጥ​ለኝ።


የውኃ ማዕ​በል አያ​ስ​ጥ​መኝ፥ ጥል​ቁም አይ​ዋ​ጠኝ፥ ጕድ​ጓ​ዶ​ችም አፋ​ቸ​ውን በኔ ላይ አይ​ክ​ፈቱ፤


ለአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም በሰ​ቂማ ግንብ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ አንድ ሆነው እንደ ተሰ​በ​ሰቡ ነገ​ሩት።


ሕዝ​ቡም ሁሉ እን​ዲሁ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው የዛ​ፉን ቅር​ን​ጫ​ፎች ቈረጡ፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንም ተከ​ት​ለው በም​ሽጉ ዙሪያ አኖ​ሩ​አ​ቸው፤ ምሽ​ጉ​ንም በላ​ያ​ቸው በእ​ሳት አቃ​ጠ​ሉት፤ የሰ​ቂ​ማም ግንብ ሰዎች ሁሉ ደግሞ አንድ ሺህ የሚ​ያ​ህሉ ወን​ድና ሴት ሞቱ።


አቤ​ሜ​ሌ​ክም ወደ ግንቡ ሄደ። እነ​ር​ሱም ተዋ​ጉት። አቤ​ሜ​ሌ​ክም በእ​ሳት ሊያ​ቃ​ጥ​ለው ወደ ግንቡ ደጅ ቀረበ።