መሳፍንት 9:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአቤሜሌክም በሰቂማ ግንብ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ አንድ ሆነው እንደ ተሰበሰቡ ነገሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቢሜሌክም በሴኬም ግንብ ገዦች ሁሉ መመሸጋቸውን ሲሰማ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤሜሌክም በዚያ መመሸጋቸውን ሲሰማ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቤሜሌክም በሴኬም መሰብሰባቸውን ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሜሌክም በሴኬም ግንብ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ አንድ ሆነው እንደ ተሰበሰቡ ሰማ። |
አቤሜሌክና ከእርሱ ጋር ያሉትም ሕዝብ ሁሉ ወደ ሄርሞን ተራራ ወጡ፤ አቤሜሌክም በእጁ መጥረቢያ ወስዶ የዛፉን ቅርንጫፍ ቈረጠ፤ አንሥቶም በጫንቃው ላይ ተሸከመው፤ ከእርሱም ጋር ለነበሩት ሕዝብ፥ “እኔ ሳደርግ ያያችሁትን፥ እናንተም ፈጥናችሁ እኔ እንዳደረግሁ አድርጉ” አላቸው።