በነጋውም ሕዝቡ ወደ እርሻ ወጡ፤ ለአቤሜሌክም ነገሩት።
በማግስቱም የሴኬም ሕዝብ ወደ ዕርሻ ወጡ፤ ይህም ለአቢሜሌክ ተነገረው፤
በማግስቱ የሴኬም ሕዝብ ወደ ዕርሻ ወጡ፤ ይህም ለአቤሜሌክ ተነገረው፤
በማግስቱ የሴኬም ሕዝብ ወደየእርሻቸው መሄዳቸውን አቤሜሌክ ሰማ፤
በነጋውም ሕዝቡ ወደ እርሻ ወጡ፥ አቤሜሌክም ሰማ።
አቤሜሌክም በአሪማ ተቀመጠ፤ ዜቡልም ገዓልንና ወንድሞቹን በሰቂማ እንዳይኖሩ ከለከላቸው።
ሕዝቡንም ወስዶ በሦስት ወገን ከፈላቸው፤ በሜዳም ሸመቀ፤ ተመለከተም፤ እነሆም፥ ሕዝቡ ከከተማ ወጡ፤ ተነሣባቸውም፤ ገደላቸውም።